የኤርታ አሌ የእሳተ ገሞራ ነገር …

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኤርታ አሌ የእሳተ ገሞራ ላቫ ሀይቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረት እየሳበ ይገኛል

በኢትዮጵያ በአፋር ክልል ዳናኪል ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘውና ንቁ ከሆኑ የምድር እሳተ ገሞራዎች አንዱ የሆነው የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ላቫ ሀይቅ በሳይንቲስቶችና በቱሪስቶች ዘንድ የላቀ ትኩረት እያገኘ መሆኑ ተገልጻል።

የሦስቱ አህጉራዊ ቴክቶኒክ ፕሌቶች እንቅስቃሴ በሚታይበት በዚህ ስፍራ የሚገኘው ኤርታ አሌ፣ አህጉራት እንዴት እንደሚከፈሉና ምድር በውስጧ ያለውን ሙቀት እንዴት እንደምትገልጽ የሚያሳይ ህያው የተፈጥሮ ቤተ-ሙከራ ሆኖ ያገለግላል።

ይህ በባሳልቲክ ጋሻ መልክ የተገነባው እሳተ ገሞራ ሁልጊዜም በሚፈላው የላቫ ሀይቁ የሚታወቅ ሲሆን፣ እጅግ ከፍተኛ በሆነ የሙቀት መጠን፣ በጨው ሜዳዎችና በጂኦተርማል እንቅስቃሴዎች የተከበበ በመሆኑ ልዩ ገጽታን ያበራክታል።

አካባቢው አፎታ የማይሰጥና አስቸጋሪ የአየር ንብረት ያለው ቢሆንም፣ ከዳሎልና ከአሳሌ ሀይቅ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ አስደናቂ የጂኦ-ቱሪዝም መስህቦች አንዱ ለመሆን ችሏል።

ዓለም አቀፍ የስነ-ምድር ተመራማሪዎች እንደሚገልጹት፣ ኤርታ አሌ ለወደፊቱ ለሚደራጀው የአፋር ጂኦፓርክ ዋነኛ የምርምርና የመስህብ ማዕከል የመሆን ከፍተኛ አቅም አለው።

ንቁ የሆነው የእሳተ ገሞራ እንቅስቃሴ፣ የላቫ ሀይቁና የምድር መሬት መሰነጣጠቅ ሂደት ጥምረት ለአካባቢው ልዩ የተፈጥሮ ቅርስነትና ለትምህርታዊ ምርምሮች ከፍተኛ ዋጋ እንዲኖረው አድርጎታል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#ertaale #afar #danakildepression #ethiopiantourism #volcano #geology #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1