ያልተጠናቀቁ ሕንፃዎችን ማከራየት የ100ሺ ብር ቅጣት ያስከትላል፡፡የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ባወጣው አዲስ የአ…

- Advertisement -
Sidebar AD

ያልተጠናቀቁ ሕንፃዎችን ማከራየት የ100ሺ ብር ቅጣት ያስከትላል፡፡
የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ባወጣው አዲስ የአደጋ ሥጋት ደኅንነት መመሪያ መሠረት፤ ግንባታቸው ሳይጠናቀቅና የደኅንነት ማረጋገጫ ሳያገኙ ሕንፃዎችን ለአገልግሎት የሚያከራዩ አከራዮች የ100 ሺሕ ብር ቅጣትና የወንጀል ተጠያቂነት ይጠብቃቸዋል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው ሕንፃዎች በዜጎች ሕይወትና ንብረት ላይ የሚያደርሱትን ከፍተኛ አደጋ ለመከላከል ነው።
በተጨማሪም መመሪያው በግንባታ ወቅት የሠራተኞች ደኅንነት መጠበቂያዎችን አለማሟላት፣ የተቆፈሩ ጉድጓዶችን አለመከለልና ምልክት አለማድረግ፣ ጠንካራ ያልሆኑ የማደላደያ ቁሳቁሶችን መጠቀም፣ እንዲሁም በቀላሉ ሊደረመሱ የሚችሉ አፈርና የግንባታ ተረፈ ምርቶችን ማከማቸት በጥብቅ ይከለክላል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2