ትዳር በፍቅር ሲገነባ እና በትግስት ሲጠበቅ እድሜው ወርቅ ይለብሳል!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ግማሽ ክፍለ ዘመን የተሻገረው የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል።

የአቶ አሊ ዑመር እና የወ/ሮ ፌሶ ሱሌ የ50ኛ አመት የፍቅር እና የጽናት ጉዞ

በፍቅር፣ በትግስት እና በመከባበር የተገነባው የትዳር ህይወት እድሜ ጠገብ ለመሆኑ ሌላው ህያው ማረጋገጫ የሆኑ ባለትዳሮች።

አቶ አሊ ዑመር እና ወ/ሮ ፌሶ ሱሌ ወርቃማውን የ50 ዓመት (ግማሽ ክፍለ ዘመን) የጋብቻ በዓላቸውን በደስታ እና በክብር አክብረዋል።

ይህ ረጅም የትዳር ጉዞ ለልጆቻቸው ብቻ ሳይሆን ለአካባቢያቸው እና ለወጣቱ ትውልድ ትልቅ የምሳሌነት እና የተስፋ ምንጭ ሆኗል።

ጥንዶቹ በአምስት አስርት ዓመታት የትዳር ዘመናቸው፦

8 ልጆችን ኮትኩተው አስተምረው እና ለወግ ማዕረግ አብቅተዋል።

የትዳራቸው በረከት ተተትርፎ 17 የልጅ ልጆችን ለማየት እና ለመሳም በቅተዋል።

አቶ አሊ እና ወ/ሮ ፌሶ በጋራ ያሳለፏቸው 50 ዓመታት ትዳር በፈተናዎች እና በደስታዎች ውስጥ አብሮ በመቆም በመከባበር እና አታላይ ባልሆነ እውነተኛ ፍቅር ላይ ሲመሰረት ለትውልድ የሚሻገር ጠንካራ መሶብ እንደሚሆን ነው።

ለአቶ አሊ ዑመር እና ለወ/ሮ ፌሶ ሱሌ እንኳን ለ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ የጋብቻ በዓላችሁ አደረሳችሁ እያልን በቀጣይም አምላክ ረጅም እድሜ ከጤና እና ከበለጠ ደስታ ጋር እንዲሰጣችሁ መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን!

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#ኢትዮጵያ #ጋብቻ
#ፅናት #ትዕግስት
#50ኢዮቤልዩ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: