ካለን ላይ በማካፈል ለተቸገሩ እንድረስ፣የበረከት ስራን እንስራ

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ታላቁ ጻድቅ አባት አባ ሣሉሲ ዜና ሕይወታቸው እጅግ ከሚያስገርሙ ገዳማውያን አንዱ ናቸው። መጽሐፈ ስንክሳር እንደሚገልጸው የዘመነ ከዋክብት ፍሬ ከሚባሉት ጻድቃን አንዱ ሲሆኑ በነበሩበት ገዳም የሚታወቁት ግን ‘የማይጾመው፣ የማይጸልየው፣ ሥራ ፈቱ መነኩሴ’ በሚል ነበር።

ገዳሙ ውስጥ ከሚኖሩ መነኮሳት መካከል አንድም ቀን ቢሆን አባ ሣሉሲ ሲጸልዩና ሲሰግዱ ያያቸው የለም። ሁሌ ብቻ እንደ ሞኝ ቁጭ ብለው ያኝካሉ። በዚህ ምክንያትም ሥጋ ወደሙን ወስደው አያውቁም።

አንድ ቀን ግን በገዳሙ በዓል ላይ አበምኔቱና መነኮሳቱ መከሩ። “አባ ሣሉሲን አሥረን አውለን ቢያንስ ለቁርባን እናብቃቸው።” ሲሉ ወሰኑ። በውሳኔው መሠረትም በጧት ሒደው ጻድቁን አሠሯቸው።

አባ ሣሉሲም “ፍቱኝ ቁርሴን ልብላበት?” ሲሉ ተቆጡ። መነኮሳቱ ግን “ሳትቆርብ አንለቅህም።” አሏቸው። በዚህ ጊዜ ጻድቁ ቆባቸውን አውልቀው “እመቤቴ የሰው ልጅስ ጨካኝ ነው። አንቺ ግን ርኅርኅት ነሽ።” ብለው በቆባቸው ግድግዳውን ቢመቱት ለሁለት ተሰነጠቀ።

እርሳቸውም ሁለት ክንፍ አውጥተው በረው ተሰወሩ። ባዩት ነገር የደነገጡ መነኮሳት እያለቀሱ ሦስት መቶ ጊዜ “እግዚኦ…..” አሉ። በዚህ ጊዜ የጻድቁን ቆብ አገኙ። በዚህች ቆብም አጋንንትን አሳደዱ ተአምራትንም ሠሩ።

አባ ሣሉሲ ግን ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ በተመስጦ በልባቸው ስለሚጸልዩና ይህ ቅድስናቸው እንዳይታወቅ ነበር የሚጥሩት፡፡ በጧት ተነስተው የሚያኝኩትም ደረቅ ሣር እንጂ ምግብ አልነበረም። ከውዳሴ ከንቱ መራቅ ማለት ይሔው ነው።

ስንቶቻችን ጥቂቷን በጎነታችን ሰው ሁሉ እንዲያውቅልን ስንጥር ገዳማውያን ግን ጤዛ ልሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ግርማ ሌሊቱን ጸብአ አራዊቱን ታግሰው ሀገርንና ሕዝብን ሌት ተቀን በጸሎት ሊያስምሩ እየተጉ መንፈሳዊ ጸጋና ክብር ሲያገኙ ትሕትናቸው ይበልጥ ከፍ ይላል፡፡

“ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም” በከባድ ንፋስና ዝናብ ምክንያት ቤተ መቅደሱ ፈርሶ ይገኛል፣ መነኮሳቱም በድርቅና በርሃብ ከባድ ፈተና ውስጥ ሆነው ድጋፋችንን እየጠበቁ ነውና የድጋፍ እጃችንን እንዘርጋላቸው።

በረሃብ ውስጥ መኖር የዕለት እንጀራን ብቻ ማጣት ሳይሆን ጤናን፣ ክብርንና ተስፋን የሚፈታተን አስከፊ ሕይወት ነውና ካለን ላይ በማካፈል ገዳማዊያኑን እንርዳ፣ለነፍሳችንም ስንቅን እንያዝ።

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡- 1000766349227

አቢሲንያ ባንክ ፡- 262281132

ለበለጠ መረጃ:- 0944672222 ወይም 0916106921






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2