የክልል ልዩ ኃይል ይፍረስ፣ሀገር አቀፍ ሚሊሻ ይደራጅ የሚሉ አጀንዳዎች ቀርበዋል‼️
“በተቋማት ግንባታ፣ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች” አጀንዳ ውስጥ ከተካተቱ ንዑስ አጀንዳዎች መካከል “የጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት ነጻነት፣ ገለልተኝነት እና አደረጃጀት” ጉዳይ ይገኝበታል።
በንዑስ አጀንዳው አማካኝነት ምክክር ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል የክልል ልዩ ኃይሎች ጉዳይ የሚገኝበት ሲሆን፤ አሁንም የልዩ ኃይል አደረጃጀትን ያላፈረሱ ክልሎች መኖራቸው በምክክር ሂደቱ መነሳቱን ምንጮች ነግረውናል።
ምንም እንኳን የክልሎች የልዩ ኃይል አደረጃጀት እንዲፈርስ የተወሰነ ቢሆንም፤ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ እና አፋር ክልሎች በተለያየ መልክና ስያሜ የልዩ ኃይል ሠራዊታቸውን ሳይበትኑ ማስቀጠላቸውን ያነሱ ተመካካሪዎች፤ ውሳኔው በሁሉም ክልሎች በዕኩልነት ተግባራዊ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ሰምተናል።
የሶማሌ ክልል ባለድርሻ አካላትን ወክለው በጉባኤው እየተሳተፉ የሚገኙ ተመካካሪዎች፤ ከክልሉ ጋር በሚጎራበቱ የሶማሊያ አካባቢዎች የአልሸባብ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን በማንሳት ክልሉ አሸባሪዎችን ለመታገል የልዩ ኃይል አደረጃጀቱን እንዲያስቀጥል ጠይቀዋል። ይሁንና የሁሉም ልዩ ኃይሎች አደረጃጀት እንዲፈርስ የቀረበው ምክረ ሀሳብ ሚዛን መድፋቱን ሰምተናል።
በዚህም እንደ ሶማሌ ባሉ ክልሎች የአካባቢውን ቋንቋ እና ስነ ልቦና የሚያውቁ የፌደራል ጸጥታ አካላት እንዲሰማሩ ምክረ ሀሳብ መቅረቡን ምንጮች ጠቁመዋል።
ክልሎች የልዩ ኃይል አደረጃጀታቸውን ማፍረሳቸውን ቢገልጡም፤ በፖሊስና አድማ ብተና ስም ዘመናዊ ትጥቆችን የታጠቀ ሰራዊት አደራጅተዋል የሚል ሀሳብ የሰነዘሩ ተመካካሪዎች በበኩላቸው፤ የክልሎችን የመሳሪያ እና የሰራዊት አቅም የሚቆጣጠር አደረጃጀት በፌደራል ደረጃ እንዲቋቋም ምክረ ሀሳብ ማቅረባቸውን ሰምተናል። እነዚህ ምክረ ሀሳቦች የሥራ ቡድኑ ውሳኔ እንዲያሳልፍባቸው የቀረቡ ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪ ወጥ በሆነ መንገድ አገር አቀፍ ሚሊሻ እንዲደራጅና ለሚሊሻ አባላት ወርሃዊ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ምክረ ሀሳብ ቀርቧል። ዋዜማ
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.