#Ethiopia | የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርናም ከባህር ማዶ እረፍታቸው ከተመለሱ በኋላ የዜጎችን እውነተኛ የዕለት ተዕለት ፈተናዎች በቅርበት ለመረዳት በመላው ብሪታንያ በሚገኙ ከተሞችና መንደሮች ጉብኝት ማድረግ ጀምረዋል።
በደቡብ ዌልስ ፖርት ታቦት የሚገኙትን እና በቅርቡ የብረት ማቅለጫ ፋብሪካ በመዘጋቱ የተነሳ ከሁለት ሺህ በላይ የሥራ እድል ያጡ ዜጎችን ጨምሮ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በቀጥታ በመገናኘት ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጉብኝታቸው ወቅት ጋዜጣ ላይ ለሚወጣ ፎቶግራፍ ሳይሆን ህዝቡን “በእርግጥ ሕይወታችሁን የተሻለ የሚያደርገው ምንድን ነው?” የሚል ጥያቄ በመጠየቅ የተሰማቸውን ብሶት ለማዳመጥ መወሰናቸውን ተናግረዋል።
ይህ ጉብኝት መንግሥት የኑሮ ውድነትን ለማቃለል እያደረጋቸው ካሉት የመጀመሪያ የፖሊሲ እርምጃዎች ጋር ተያይዞ የተከናወነ ነው። ከእነዚህም መካከል ከጥቅምት አንድ ጀምሮ የኤሌክትሪክ ቢል ላይ የሚጣለውን ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በማንሳት ለየቤተሰቡ አማካይ 45 ፓውንድ ማስቀረት እና ከጥር ጀምሮ የህዝብ ማጓጓዣ አውቶቡስ ታሪፍን በሁለት ፓውንድ መገደብ ይገኙበታል።
በተጨማሪም በሚቀጥለው ሳምንት በንግድ ቤቶች የሚደረጉ አሳሳች የዋጋ ቅናሾችንና የማታለያ አሰራሮችን ለመግታት የሚያስችሉ አዳዲስ መመሪያዎች ይፋ እንደሚደረጉ ተጠቅሷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ጉብኝት ከህዝቡ የሚሰበስቧቸውን አስተያየቶች በዓመቱ መጨረሻ ይፋ ለሚደረገው የአገሪቱ የአሥር ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ በግብዓትነት እንደሚጠቀሙበት አስታውቀዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.