#Ethiopia | በሸገር ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት እና በሲያትል አካዳሚ መካከል በተደረገው ስምምነት መሠረት ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለአራት ወራት የተሰጠው የቴክኖሎጂ ስልጠና መጠናቀቁን ተክተሎ በኤቨረስት አካዳሚ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን እና ውድድር ተካሂዷል።
ተማሪዎቹ በስልጠናው ወቅት በኮዲንግ፣ በሮቦቲክስ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በኮምፒዩቲንግ፣ በኤሌክትሮኒክስ ዲዛይን እና በፕሮግራሚንግ ዘርፎች የቀሰሙትን የላቀ እውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ችሎታቸውን ለዕይታ አቅርበዋል።
ይህም ስራቸው ለሀገራችን የቴክኖሎጂ እድገት ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ እና ወደፊት በዘርፉ አዎንታዊ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉበትን አቅም ያሳየ እንደሆነ ተገልጿል።
በመድረኩ የሸገር ከተማ አስተዳደር፣ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለተማሪዎቹ የፈጠራ ስራዎች ልዩ አድናቆት የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ተስፋ ሰጪ ለሆኑት እነዚህ ወጣቶች ያልተቋረጠ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተረጋግጧል።
በተጨማሪም ስልጠናውን በማዘጋጀትና በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከተው የሲያትል አካዳሚ፣ የስልጠናውና የፕሮጀክቱ ሀሳብ አመንጪ እንዲሁም የትምህርት ቤቱ ባለቤትና ማናጀር ለሆኑት ለአቶ መንግስቱ ወዳጄ ልዩ ምስጋና እና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በዚሁ ዝግጅት ላይ የከተማው አስተዳደር እና የትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች የአድናቆት መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የዘርፉ ባለሙያዎችም ተገኝተው ልምዳቸውን አክፍለዋል።
የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለሀገር እድገት ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ መሰል ድጋፎች ለኢትዮጵያ ወጣቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አፅንኦት ተሰጥቶበታል።
በመጨረሻም በውድድሩ የላቀ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራቸውን ላቀረቡ ተማሪዎች የሽልማት እና የእውቅና መስጠት ሥነ ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን ታናናሽ ህፃናትም የወደፊት ራዕያቸውን እንዲቀርጹና ፍላጎት እንዲያዳብሩ የመድረኩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል።
#shegercity #seattleacademy #coding #robotics #artificialintelligence #ethiopianews #technologyinethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen








No comments yet.