በዓለም አቀፍ የፍትህ ችሎት የኢትዮጵያን የአባይ ወንዝ ፍትሐዊ የመጠቀም መብት የሚያስከብርና የካሳ ጥያቄ የሚያነሳ ስትራቴጂካዊ

- Advertisement -
Sidebar AD

በዓለም አቀፍ የፍትህ ችሎት የኢትዮጵያን የአባይ ወንዝ ፍትሐዊ የመጠቀም መብት የሚያስከብርና የካሳ ጥያቄ የሚያነሳ ስትራቴጂካዊ ጥናት ተዘጋጀ

#Ethiopia | ሀገራችን ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን ፍትሐዊና ምክንያታዊ የመጠቀም መብት በዓለም አቀፍ የፍትህ ችሎት ለማስከበር እንዲሁም በዚሁ ሰበብ ለደረሱባት ጉዳቶች የካሳ ጥያቄ ለማቅረብ የሚያስችል ባለ 160 ገጽ አገራዊ ስትራቴጂካዊ ጥናት ተዘጋጅቶ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት እና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀርብ እንደሆነ ተገለጸ።

በኢንጂነር አልጣህ ረጋስ ታቦር የቀረበው ይህ አጠቃላይ ጥናት በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የአምስት ዓመት ሕጋዊ ጥበቃ የተደረገለት ሲሆን በማመልከቻ ቁጥር LTR/W/11627/2018 እና በምዝገባ ቁጥር 1/2/5/00122 ይፋዊ ዕውቅና ተሰጥቶታል።

ይህ ሰነድ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን የሉዓላዊነት መብት በዓለም አቀፍ ሕግ፣ በዲፕሎማሲ፣ በቴክኒክ ማስረጃዎችና በሰላማዊ የሕግ ተቋማት አማካኝነት እንዴት ማስጠበቅ እንደሚቻል በጥልቀት ያብራራል።

ጥናቱ ሀገራዊ ጥቅምን ማዕከል በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን፣ ቀጣይነት ያለው ትብብርንና የትውልድን መብት ለማረጋገጥ እንዲሁም በሀገሪቱ ላይ ለደረሱ ሁሉን አቀፍ ጉዳቶች የካሳ ጥያቄ ማዕቀፍን አዘጋጅቶ ያቀርባል።

ሰነዱ የሕግ መሠረቶች፣ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች፣ ስትራቴጂካዊ የውሳኔ ሃሳቦች እና አባሪዎች የተሰኙ አራት ዋና ዋና ክፍሎችን ያካተተ ሲሆን ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ስትከተለው የቆየችውን ውጤት አልባ የድርድር መንገድ በመቀየር መብቷን በዓለም አቀፍ የፍትህ ችሎት ፊት በጽናት እንድትጠይቅ የሚያስችል አዲስ ፍኖተ ካርታ ነው።

የጥናቱ አዘጋጅ ኢንጂነር አልጣህ ረጋስ ታቦር በ1995 ዓ.ም ከአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በመስኖ ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን ባለፉት 20 ዓመታት በላይ በውሃ ምህንድስና እና ኮንስትራክሽን ዘርፍ በሙያቸው አገልግለዋል።

በቀድሞው የውሃ ስራዎች ዲዛይን እና ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ በተለያዩ የውሃ ፕሮጀክቶች ላይ እስከ 2002 ዓ.ም የሰሩ ሲሆን ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት በግል የምህንድስና አማካሪነት ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#nile #abbay #ethiopianrights #icj #internationallaw #waterengineering #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2