የአሌክስ ፈርጉሰን አልጋ ወራሽ ልሆን ተቃርቤ ነበር

- Advertisement -
Sidebar AD

~ጆዜ ሞሪንሆ

#Ethiopia | ጆዜ ሞሪንሆ በ2013 ዓ.ም ሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ለመተካት ተስማምተው እንደነበር ይፋ አደረጉ።

በፈረንጆቹ 2013 ጆዜ ሞሪንሆ ከሪያል ማድሪድ ከተለያዩ በኋላ የሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ቦታ ለመተካት ተስማምቼ ነበር ሲሉ ገልጸዋል።

በጊዜው ማንችስተር ዩናይትድን ለመረከብ የመጀመሪያ ስምምነት አድርገው እንደነበርም ይፋ አድርገዋል።

ነገር ግን በወቅቱ ውሳኔያቸውን በፍጥነት በመቀየር ወደ ቼልሲ ለማቅናት መወሰናቸውንም አረጋግጠዋል።

በ2013 ከሪያል ማድሪድ ስወጣ ሰር አሌክስ ፈርጉሰንን ተክቼ ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል ተስማምቼ ነበር።

ጥያቄው በጣም አክብሬ ነው የተቀበልኩት ምክንያቱም ማንችስተር ዩናይትድ እጅግ ትልቅ ክለብ በመሆኑ ሲሉ ተናግረዋል።

በወቅቱ ሞሪንሆ ለቼልሲ የሰጡትን ቃል ላለማፍረስ ሲሉ ወደ ኦልድ ትራፎርድ የማመራቱን እድል ሳይጠቀሙበት መቅረታቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Manchesterunited
#RealMadrid
#JoséMourinho #SirAlexFerguson


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: