#Ethiopia | በአዲስ አበባ በሚገኘው ጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል የ26 ዓመት ወጣት እናት በአንድ ጊዜ አራት ሕፃናትን በሰላም ማገላገሉን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ።
በአሁኑ ወቅት እናትየዋና አራቱም ጨቅላ ሕፃናት በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።
የሕክምና ሂደቱን በበላይነት የመሩት የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅና የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር እሸቱ ታደለ እንደገለጹት፣ የእርግዝናው ሁኔታ አስቀድሞ በክትትል በመታወቁ እናቲቱ ከወሊድ ቀኗ አንድ ወር በፊት በሆስፒታሉ ተኝታ ሌት ተቀን ጥብቅ ክትትል ሲደረግላት ቆይታለች።
የሆስፒታሉ የሕክምና ቡድን በከፍተኛ የሕክምና ቴክኖሎጂና አጋዥ መሳሪያዎች የታገዘ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ቀዶ ሕክምናውን በስኬት ማጠናቀቅ ችሏል።
ዶክተር እሸቱ አክለውም ይህ አጋጣሚ “እናት ጤና፤ ልጅም ደህና” የሚለውን ሀገራዊ የጤና መርሕ በተግባር ለማዋል የተከናወነና ለእናቶችና ሕፃናት ጤና የተሰጠውን ትልቅ ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen







No comments yet.