የዕድሜ ደመራ መጽሐፍ የፊርማ ሥነ ሥርዓት በአብርሆት ቤተ መጽሐፍት በደመቀ ሁኔታ ተከናወነ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | አዲስ አበባ — ደራሲ ውድአላት ገዳሙ ለ21 ዓመታት ስትደክምበት የቆየችውን “የዕድሜ ደመራ” የተሰኘ አዲስ መጽሐፏን ለአንባቢዎች ለማቅረብ ያለመ የፊርማና የፎቶግራፍ ሥነ ሥርዓት በአብርሆት ቤተ መጽሐፍት አካሄደች።

ተወዳጅ ሚዲያ ያስተባበረው የቅድመ ግዥ (Pre-order) ቻሌንጅ ውጤት የሆነው ይህ መርሐ ግብር፣ ደራሲዋ ከኅትመት በፊት ቀድመው ለገዙና በዕለቱ በቦታው ለተገኙ በርካታ አንባቢዎቿ፣ ወዳጆቿና አድናቂዎቿ በፊርማዋ ያሸበረቁ መጻሕፍትን በክብር ያበረከተችበት ነበር።

በሁነቱ ላይ የጥበብና የትምህርት ተቋማት ታዋቂ ግለሰቦች የተገኙ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል
* ጸሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ እና ደራሲ ፀሐይ መልአኩ
* ኢምሬትስ ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈራ
* ኢንጂኒየር ደራሲ ባንትይሁን ትእዛዙ (የሰው ደግፍ ድርጅት መሥራች) ይገኙበታል።

ታዳሚዎቹ ደራሲ ውድአላት ገዳሙ የጽናት ተምሳሌት መሆኗን ገልጸው፣ ለዚህ ስኬት ከጎኗ በመቆም ላገዟት ባለቤቷ መምህር ያሳቡ ያሬድ እና ለቤተሰቧ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ደራሲዋ ባስተላለፈችው መልእክት መጽሐፉ በ1997 ዓ.ም. መፀነሱንና ልክ እንደ 4ኛ ልጅ አምጣ የተገላገለችው ሥራዋ መሆኑን ጠቅሳ፣ ለመጽሐፉ ጥራትና መውጣት አስተዋጽኦ ላደረጉት የሜሮን ማተሚያ ድርጅት፣ ለአብርሆት ቤተ መጽሐፍት፣ ለአስተናጋጁ ቴምር ፕሮፐርቲስ እንዲሁም ለተወዳጅ ሚዲያ መሥራች ጋዜጠኛ እዝራ እጅጉና ሌሎች ባልደረቦቿ የላቀ ምስጋናዋን አቅርባለች።

የቀጣይ መርሐ ግብርና መረጃ፡
* ይፋዊ የምረቃ ሥነ ሥርዓት፡ በመጪው የጷጉሜን ወር በአድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል።
* መጽሐፉን ለማዘዝ፡ በስልክ ቁጥር 0911 34 06 16 ደውለው ማግኘት ይችላሉ።






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: