ባለቤቱን በመግደል የተከሰሰው ግለሰብ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።
በአዲግራት ከተማ ቀበሌ 06 ዞን 6 ነዋሪ የሆነው አቶ ሳምሶም ሓጎስ አብርሃ የተባለው ተከሳሽ የሁለት ልጆቹ እናት የሆነችውን የ22 ዓመቷን ባለቤቱን ወይዘሮ ቅሳነት ተሾመን መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በፈፀመው አሰቃቂ የነፍስ ግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ነው በ21 አመት ከ 3 ወር ፅኑ እስራት የተቀጣው።
የምስራቅ ትግራይ ዞን ዓቃቤ ሕግ አቶ መሓሪ እንደገለፁት ተከሳሹ በከባድ የነፍስ ግድያ ወንጀል ተከሰሶ ጥፋተኛነቱ ከተረጋገጠ በኋላ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈፅሞ የማያውቅ እና ቤተሰብ አስተዳዳሪ የነበረ መሆኑን እንደ ማቅለያ እንዲሁም ሁለት የማክበጃ ነጥቦችን በመያዝ ሕግን መሰረት ያደረገ ውሳኔ ሰጥቷል ብለዋል።
በአዲግራት ከተማ የሴቶች ማህበር ሊቀመንበር እና የሴቶች ጉዳይ ፅህፈት ቤት በበኩሉ በአሁኑ ወቅት በሴቶች ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃት እና ነፍስ ግድያ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ገልጾ የሕግ ባለሙያዎች ግንዛቤ እንዲፈጥሩ እና ማህበራትም ተጎጂዎች ፈጣን ፍትህ የሚያገኙበትን ሁኔታ እንዲያመቻቹ ጥሪ አቅርቧል።
በሌላ በኩል የተበዳይ ቤተሰቦች ፍትህ ለማግኘት ረጅም ጊዜ እንደወሰደባቸው በመግለፅ የፍርድ ቤቱን የቅጣት ውሳኔ እንዳልተቀበሉትና ደስተኛ እንዳልሆኑ መግለፃቸውን ብስራት ከአዲግራት ከተማ የኮሚኒኬሽን ፅሕፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።
@Seledadotio

No comments yet.