— አቶ ዘላለም መርዓዊ
#Ethiopia | አቶ ዘላለም መርዓዊ ከመሪ ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ በሀገሪቱ በሚመረቱ የግብርና ምርቶች ላይ በቂ የዕሴት መጨመር (value addition) ሥራ አለመሰራቱ ለሀገር እድገት እንቅፋት መሆኑን ገለጹ።
በአሁኑ ወቅት በርካታ አርሶ አደሮች አቮካዶን በጥሬው ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በማሰብ ዘር ተክለው የሚያመርቱ ቢሆንም ምርቱን በጥሬው ከመብላትና ከመሸጥ ባለፈ የማኑፋክቸሪንግ እና የዕሴት መጨመር ሥራ ካልተሰራ ሀገር ሊያድግ እንደማይችል አስገንዝበዋል።
በምሳሌነትም በወለጋ አካባቢ በምርት ወቅት እጅግ በርካታ ማንጎ ከዛፍ ላይ ወድቆ በመበስበስ ለብክነት እንደሚዳረግ የጠቆሙት አቶ ዘላለም በጥሬው የሚባክኑ እንደ አቮካዶና ማንጎ ያሉ የፍራፍሬ ምርቶችን ወደ ጭማቂ፣ የአቮካዶ ዘይት፣ የቆዳና የፀጉር ማለስለሻዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ውጤቶች በመቀየር ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጥቅም ማግኘት እንደሚቻል ጠቁመዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.