በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጉባኤ ላይ የተሳተፉ የዲያስፖራ አባላት የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጎበኙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I በሀገራዊ ምክክር መድረክ ላይ ላለፉት ሶስት ሳምንታት ሲሳተፉ የቆዩ የዲያስፖራ አባላት ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት እና ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተዘጋጀ ልዩ የጉብኝት መርሃ ግብር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።

የዲያስፖራ አባላቱ በጉብኝታቸው ወቅት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ ወደ ሙሉ ስራ በመግባቱ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ከግብ ለማድረስ ለተደረገው ቁርጠኝነትና አመራር አድናቆታቸውን ለግሰዋል። ባለፈው መስከረም ወር ሙሉ በሙሉ ተመርቆ ስራ የጀመረው ህዳሴ ግድብ የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ 50 በመቶ ያህሉን የሚሸፍን ሲሆን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ መንደሮችን ከብሔራዊ የኃይል መረብ ጋር ማገናኘት ተችሏል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት፣ የውጭ ሀገራት ኤምባሲዎች እና የዲያስፖራ ማህበረሰቦች ባደረጉት የተቀናጀ እንቅስቃሴ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ብቻ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ 3.2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም በጅቡቲ ለሚገኘው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ፕሮጀክት 400 ሺህ ዶላር በቦንድ እና በስጦታ መልክ ማሰባሰብ ተችሏል።

የጉብኝት መርሃ ግብር ላይ የተሳተፉ የዲያስፖራ አባላት በጅቡቲ ለሚገነባው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ትምህርት ቤት ግንባታ የሚሆን ከ1.7 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ በቦታው ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ይህም የዲያስፖራው ድጋፍ ከፋይናንስ ባለፈ ለሀገርና ለወገን ያለውን አለኝታነት ያረጋገጠ መሆኑ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍፁም አረጋ ገልጿል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: