#Ethiopia | የኡጋንዳ መንግሥት የዜጎችን የሥራ ምርታማነት ለማሳደግ እና የጠዋት የአልኮል መጠጥ አጠቃቀምን ለመግታት ሲል መጠጥ ቤቶችና የአልኮል መሸጫ ቦታዎች በሥራ ቀናት ከቀኑ 9 ሰዓት በፊት ዝግ ሆነው እንዲቆዩ አዘዘ።
የሀገሪቱ የአካባቢ መንግሥት ሚኒስቴር ባስተላለፈው አዲስ መመሪያ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች በማንኛውም ጊዜ አልኮል መሸጥ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
ይህንን አዲስ አሰራር የአካባቢው አስተዳደሮችና የጸጥታ አካላት በጥብቅ እንዲያስፈጽሙ የታዘዙ ሲሆን መመሪያውን በሚጥሱ ዜጎች ለእስር ተቋማቱም ላይ የንግድ ቦታዎችን እስከ ማሸግ የሚደርስ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.