ምንድን ነው የሚባለው ? ፍትህስ የሚጠየቀው ከማን ነው ? …. እንደወጡ መቅረት ፣ ፎቶ እያነሱ በየመንገዱ መረሸን የዚህን

- Advertisement -
Sidebar AD

ምንድን ነው የሚባለው ? ፍትህስ የሚጠየቀው ከማን ነው ? …. እንደወጡ መቅረት ፣ ፎቶ እያነሱ በየመንገዱ መረሸን የዚህን ያህል ቀላል ነገር ይሁን ?

ወላህ ይሄን ፎቶ አይቶ አለመረበሽ ፣ አለመታመም አይቻልም። ህመማቸው ፣ ስቃያቸው ፣ ተስፋ መቁረጣቸው በሙሉ ይጋባል። ድንጋጤያቸውን ፊታቸው ይናገራል። የሚያዝኑላቸው ፣ የሚራሩላቸው ሰዎች እጅ ላይ እንዳልወደቁ ታውቋቸዋል። ከሰው ልጅ ጋር ሳይሆን ፣ ከሞት ጋር እንደተፋጠጡ አይናቸው ይናገራል….

ከቤታቸው ሲወጡ ይሄ እንደሚጥማቸው እነሱም በፍፁም አላሰቡም። ወደ ተሻለ ህይወት እየመጡ እንደሆነ ተሰምቷቸው ይሆናል። እንደኛው እየሳቁ ይሆናል። እንደኛው እየተጨዋወቱ ይሆናል። እንደኛው ስለነገ እያቀዱም ይሆናል። ተስፋ ነበራቸው። ምኞት ነበራቸው። የሚያግዟት እናት ፣ የሚጦሩት አባት ፣ የሚያሳድጉት ልጅም ይኖራቸዋል….

ከተሳፈሩበት መኪና ውስጥ መታወቂያቸውን አይተው ሲያስወርዷቸው ፣ ከሌሎች ተሳፋሪዎች ሲነጥሏቸው ፣ ደም በደም እስኪሆኑ ሲደበድቧቸው ፣ አስቀምጠው ፎቶ ሲያነሷቸው ምን ተሰምቷቸው ይሆን ? ምንስ እያሰቡ ነበር ? ይሄን የልጆቿን ፎቶ የምታይ እናትስ በምን ትፅናናለች ? ምንስ አበርትቷት እዚች የተረገመች ምድር ላይ ትኖራለች ?

Via mustajib


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: