በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጅኦስፓሻል ኢንስቲቲዩት የጆኦ ደሲ እና ጅኦ ዳይናሚክስ ኦፊሰር አቶ ወንድ ወሰን ደሴ የመሬት መንቀጥቀጡ ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ የተከሰተ መሆኑን ገልፀዋል።
እሁድ ዕለት በመተሐራ የተከሰተው የመሬትመንቀጥቀጥ ከአንድ ዓመት በኋላ በድጋሚ የተከሰተ መሆኑን ገልፀው መንስኤውም በከርሰ ምድር ባሉ ቋጥኝ አለቶች ስር የሚገኝ የማግማ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ እንደሆነ ተናግረዋል።
ማኅበረሰቡን እንዳይጎዳ የቅድመ ዝግጅት እና የግንዛቤ ሥራዎችን ኢንስቲቲዩቱ እንደሰራም አንስተው ክትትል የሚያደርግ ማዕከል ተቋቁሞ ባለሙያዎችን በመላክ ሳይንሳዊ ጥናት እየተካሄደ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም የማኅበረሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች መሰራታቸውን አክለው ኢንስቲቲዩቱም የመሬት መንቀጥቀጥ ሂደቱን እንደሚከታተል አሳስበዋል።
በመተሐራ እና አካባቢው የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀት በሬክተር ስኬል 4.6 እንደተመዘገበ የወጣው መረጃ ያመለክታል።
#አሐዱ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.