በኮሎምቢያ የተከሰተው ግዙፍ የመሬት መንቀጥቀጥ የ132 ሰዎች ህይወትን ቀጠፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

በኮሎምቢያ ጮኮ ግዛት ሳን ሆሴ ዴል ፓልማር አካባቢ የተከሰተው በሬክተር ስኬል 7.4 የሚለካ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ በካሊ፣ ማኒዛሌስ እና ፔሬራ ከተሞች ላይ አሰቃቂ ውድመት አድርሷል።

እስካሁን በተረጋገጠው መረጃ መሠረት ቢያንስ የ132 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፣ የፍለጋ እና አድን ስራው ሲቀጥል የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል።

ከዚህ በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ፈርሰዋል ወይም ከፍተኛ ጉዳት አስተናግደዋል።
የአሜሪካ የጂኦሎጂካል USGS እንደገለጸው የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው 110 ኪሎ ሜትር ያህል በሆነ ጥልቀት ውስጥ የመሬት የላይኛው ቋጥኝ ክፍሎች (Crusts) አግድም አቅጣጫ እርስ በእርስ በመፋቀሳቸው (strike-slip faulting) ምክንያት ነው።

ይህ አደጋ በጎረቤት ቬኔዙዌላ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ካቀጠፈውና ከ58,000 በላይ ህንጻዎችን ካደቀቀው የመሬት መንቀጥቀጥ ከአንድ ወር በኋላ የተከሰተ ነው።

በሁለቱ ሀገራት የመሬት መንቀጥቀጦች መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት ስለመኖሩ በቂ ማስረጃ ባይኖርም፣ የሳይንስ ሊቃውንት ግን በአንድ የመሬት ስብራት ላይ የሚፈጠር ጫና ወደ አቅራቢያው ስብራት የመሸጋገር (Seismic stress transfer) እድል እንዳለው ያመላክታሉ።





Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2