ቡርኪና ፋሶ በባህላዊ ጨርቃ ጨርቅ የተሰሩ አዳዲስ የወታደራዊ አልባሳትን ይፋ አደረገች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ቡርኪና ፋሶ የሀገሯን ባህላዊ እሴትና ማንነት የሚያንፀባርቁ ሙሉ በሙሉ ከአገር በቀል የባህል ጨርቃ ጨርቅ የተሰሩ አዳዲስ የወታደራዊ ሰልፍ አልባሳትን ለሹም መኮንኖቿ ይፋ አደረገች።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንትና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ካፕቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ይፋ ያደረጉት ይህ አልባሳት ከምስራቃዊቷ ጉልሙ ክልል “ሴንሴንጉ” ከተሰኘው ባህላዊ የሸማ ምርት የተዘጋጀ ሲሆን መቶ በመቶ በሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃና ዲዛይን የተመረተ ነው።

​ይህ አዲስ የወታደር አልባሳት የሀገሪቱን የጀግንነትና የአመራር እሴቶች የሚያጎሉ የካውሪ ዛጎሎች፣ ባህላዊ ቆብ፣ ብሔራዊ አርማ እና የፈረሶች ምስል ያረፈበት የወገብ ማሰሪያንም ያካተተ ነው።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ለአዲሶቹ መኮንኖች ባስተላለፉት መልእክት በሙያቸውና በአገልግሎታቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ አሳስበው በራሷ የምትተማመን ጠንካራ ብሔራዊ ጦር የመገንባትን አስፈላጊነት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: