ኤርትራ ከሕወሓት ጋር በመሆን በሉዓላዊነታችን ላይ ግልጽጥሰት እየፈጸመች ነው – አምባሳደር ጀነራል ባጫ ደበሌበሆርን  ሪቪው ላ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ኤርትራ ከሕወሓት ጋር በመሆን በሉዓላዊነታችን ላይ ግልጽ
ጥሰት እየፈጸመች ነው – አምባሳደር ጀነራል ባጫ ደበሌ
በሆርን  ሪቪው ላይ ጽሁፋቸው ያሰፈሩት አምባሳደር ጀነራል ባጫ ደበሌ፤ የኤርትራ መንግሥት ከሕወሓት አክራሪዎች ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ግልጽ ጥሰት መፈጸሙን አጋለጡ። በተለይም ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም የኤርትራ ወታደራዊ ባለሥልጣናት የሀገራቸውን ባንዲራ ይዘው ወደ ዘላንበሳ መግባታቸውና ታንኮችን ጨምሮ ከባድ መሳሪያዎችን ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ማዘዋወራቸው ሁኔታውን እጅግ አደገኛ እንዳደረገው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት ዓመታት በላይ ለቀጠናዊ ሰላም ስትል ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ትዕግስት ማሳየቷን አምባሳደሩ አስታውሰዋል። ሆኖም የኤርትራ መንግሥት ለቀረበላት የሰላም ጥሪ ጆሮ በመስጠት ፈንታ፣ ኢትዮጵያን የማዳከምና የማተራመስ የቆየ ዓላማውን አጠናክሮ መቀጠሉ ተነግሯል። በሌላ በኩል፣ የሕወሓት አክራሪዎች የትግራይን ወጣቶች በግድ በመመልመልና ለሱዳን ጦርነት በመሰልፍ ለፖለቲካ መጠቀሚያ እያዋሏቸው መሆኑ ተመላክቷል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያደረጋቸው ውስን ማዕቀቦች የኤርትራን አካሄድ መቀየር እንዳልቻሉ የገለጹት ጄኔራል ባጫ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲል አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አሳስበዋል። ኤርትራ ይህንን የጥፋት እርምጃ  ካልገታች፣ የሚመጣው ቀውስ በራሷ በኤርትራ ላይ የሀገር መፍረስ አደጋን ጨምሮ ለአጠቃላይ ቀጠናው ሰላም ከፍተኛ ስጋት እንደሚፈጥር በማስጠንቀቅ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: