የገዛ ልጅህን ገድለሃል ተብለህ ለእድሜ ልክ እስር ከርቸሌ መግባት ስሜቱ እንዴት ያለ ነው?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ኔትፍሊክስ በሳይኮሎጂካል ትሪለር እና በእንቆቅልሽ የተሞሉ ታሪኮችን ወደ ተከታታይ ፊልሞች በመቀየር ተመልካቾቹን እያስኮመከመ ነው።

“I Will Find You” የተሰኘው ድራማም ተመልካቹን ከመጀመሪያው ክፍል እስከ ፍጻሜው ድረስ ከወንበር ጠርዝ ሳይነቅል አጣብቆ የመያዝ ትልቅ አቅም ያለው በሚገርሙ የሴራ ጉንጉኖች የተሞላ ስራ ነው።

​​የታሪኩ ማዕከል ባልሰራው አስቃቂ ወንጀል—የገዛ ህጻን ልጁን በመግደል—ተከሶ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት አባት ነው። ህይወቱ በሙሉ ተስፋ በቆረጠበት፣ በጥፋተኝነት ስሜት እና በሃዘን በተሰበረበት ወቅት፣ አንድ ያልተጠበቀ መረጃ ይደርሰዋል ፧ ልጅህ በህይወት ሊኖር ይችላል!

​ይህ መረጃ የጠፋውን ተስፋ መልሶ ያለምልመዋል። እውነቱን ለማወቅ እና ልጁን ለማግኘት ሲል ከጥብቅ ጥበቃ እስር ቤት ለማምለጥ ይገደዳል። ከዚያ በኋላ ያለው ሂደት በፖሊሶችና በጠላቶቹ የሚደረግበትን አደገኛ አደን እየሸሸ፣ እውነተኛውን ወንጀለኛ ለመግለጥ የሚያደርገው ትግል ይቀጥላል።

​ታሪኩ ምንም አይነት አሰልች አካሄድ የለውም። እያንዳንዱ ክፍል አሮጌ እንቆቅልሾችን ሲፈታ፣ በዚያው ልክ ደግሞ አዳዲስ ጥያቄዎችን እና ስጋቶችን እያደራረበ ይሄዳል።

​የዋናው ባለታሪክ የአባትነት ቁርጠኝነት፣ የውስጥ ህመም እና ለነጻነቱ የሚያደርገው ትግል በተዋናዩ ድንቅ አተዋወን ስሜት ቀስቃሽነት ሆኖ የቀረበ ነው። ተመልካች ከገጸ-ባህሪው ጋር አብሮ እንዲጨነቅ እና እንዲበሳጭ የማድረግ አቅሙ ከፍተኛ ነው።

​”እውነቱን ደረስኩበት” ብለው ሲያስቡ ታሪኩ አቅጣጫውን ሙሉ በሙሉ ይቀይራል። ታማኝ ይመስሉ የነበሩ ገጸ-ባህሪያት መጠራጠር፣ እንዲሁም ያልተገመቱት ደግሞ የሴራው አካል ሲሆኑ ማየት ድራማውን ይበልጥ አጓጊ ያደርገዋል።

የፊልሙ ጨለምለም ያለ ድባብ እና በጭንቀት የተሞላው የበስተጀርባ ሙዚቃ የትሪለር ስሜቱን አጎልተውታል።

በአ​ጠቃለይ ​”I Will Find You” የእንቆቅልሽ የተሞላ፣ የፍትህ ፍለጋ እና የጽናት ተራኪ ድንቅ ሚኒ-ሲሪየስ ነው።

ታሪኩ የቤተሰብ ፍቅርንና ተስፋ አለመቁረጥን ከውጥረት ጋር አጣጥሞ ቀርቧል።
….
አትርፈው የሚዝናኑበት ነውና እንዲመለከቱት ጋበዝኖ!!

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2