#FastMereja | በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበብ ተመርቃ «ታስጨርሺኛለሽ» በተሰኘው ታዋቂ ፊልም ላይ «ኮኪ» የተባለውን ገጸ-ባህሪ በመወደድ ከፍ ያለ አድናቆት አትርፋ የነበረችው ተዋናይት ቤተልሔም (ቤቲ)፤ በ22 ዓመቷ ወደ ትዳር ከገባች በኋላ ላለፉት ሰባት ዓመታት የከፋ የቤት ውስጥ ጥቃት እና የስነ-ልቦና ጫና ይደርስባት እንደነበር በሸገር ኢንፎ ላይ ቀርባ ይፋ አደረገች።
ተዋናይቷ በማህበራዊ ሚዲያ የምታሰራጫቸው ደስተኛ ምስሎች የስነ-ልቦና እና የአካል በደሎችን ለመሸፈን የተጠቀመችባቸው የሐሰት ጭንብል እንደነበሩ የገለጸች ሲሆን፣ በእርግዝናዋ ወቅት ሳይቀር በባለቤቷ ከባድ የአካል ድብደባ ይደርስባት እንደነበር ተናግራለች። በተጨማሪም በባሏ እና በቤተሰቦቹ በኩል «ልጁ የኔ አይደለም» የሚል የተስፋፋ የጥርጣሬ ስድብ እና የስነ-ልቦና ጫና ሲደርስባት መቆየቱን ገልጻለች።
ይህ በቤት ውስጥ ይፈጠር የነበረው የማያቋርጥ ሁከትና ግጭት በልጆቿ ላይም ከባድ የስነ-ልቦና ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ በተለይም ኩነቱን ሁልጊዜ የሚያየው የሰባት ዓመት የመጀመሪያ ልጇ ለከባድ የጭንቀት ህመም ተዳርጎ በአሁኑ ወቅት በህክምና እና በመድኃኒት ለመታገዝ መገደዱ ተናግራለች።
“ሰው ናፍቆኛል ሰባት ዓመት ሙሉ ተቆልፎብኝ ኖሪያለሁ” የምትለው ተዋናይት ቤቲ አሁን ላይ ከዚህ ስቃይ ለመውጣት መወሰኗን ገልጻ፣ ምንም ዓይነት ንብረት ወይም ገንዘብ እንደማትፈልግና የምትሻው የልጆቿን ሰላም፣ ህጋዊ ከለላ እና የአእምሮ እረፍት ብቻ እንደሆነ አስታውቃለች። ጥቃቱን ተቋቁማ ወደ ብርሃን ለመውጣት ለምታደርገው ጥረትም የህግ ከለላ እና ድጋፍ እንዲደረግላት ጥሪ አቅርባለች።
Source: FastMereja









No comments yet.