ግብፅ ለአሰልጣኟ ሀውልት አቆመች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በዓለም ዋንጫው ጉዟቸው የተደነቁት የግብፅ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን ሀውልት ተቆመላቸው።

በዓለም ዋንጫው የ16ቱ ግጥሚያ ግብፅ ከአርጀንቲና ጋር ባደረገችው ውጥረት የበዛበት ጨዋታ ላይ አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን እጆቻቸውን በማንሳት የ ‘x’ ምልክት አሳይተው ነበር።

ግብጽ ለቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሆሳም ሀሰን እውቅና የሚሰጥ የመታሰቢያ ሀውልት በግብፅ ሰሜናዊ የባህር ዳርቻ ላይ አቁናለች።

ይህ ምልክት በፊፋ ደንብ መሰረት በጨዋታ ላይ የሚፈጸም ዘረኝነትን ወይም ማንኛውንም የልዩነት ጥቃት ለማመልከት የሚያገለግል ምልክት ነው።

ሆሳም ሀሰን በወቅቱ በሰጡት ማብራሪያ ምልክቱን ያሳዩት በዳኞች ውሳኔ ላይ የነበራቸውን ተቃውሞ ለመግለጽ እንጂ ዘረኝነትን ለማመልከት እንዳልሆነ አብራርተዋል።

ይህ የቆመላቸው የመታሰቢያ ሀውልት አሰልጣኙ ላሳዩት የላቀ አመራር እና በግብፅ ብሔራዊ ቡድን ታሪክ ላይ ላበረከቱት አስተዋጽኦ መሆኑ ተገልጿል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Egypt #worldcup #statue
#manager #HosamHassen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: