#Ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተቋሙን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት የሚመሩበት የአገልግሎት ዘመናቸው ለተጨማሪ አንድ ዓመት እንዲራዘም ተወሰነ።
የአቪዬሽን ጋዜጠኛ ቃለኢየሱስ በቀለ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት የአየር መንገዱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔውን ያሳለፈው ተቋሙ በአሁኑ ወቅት እያከናወናቸው ያሉትን ግዙፍ ፕሮጀክቶችና ስትራቴጂካዊ ውሳኔዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።
አቶ መስፍን ጣሰው በሕግ በተቀመጠው የመንግሥት የጡረታ መውጫ ገደብ መሠረት ቀደም ብለው ከኃላፊነታቸው መሰናበት የነበረባቸው ቢሆንም በወቅቱ የነበረውን የተቋሙን ፍላጎትና አስፈላጊነት መሠረት በማድረግ ቦርዱ የአገልግሎት ዘመናቸውን ለሁለት ዓመታት እንዲራዘም ማድረጉ ይታወሳል።
ይህ የሁለት ዓመት ገደብ ከተጠናቀቀ በኋላም ለአንድ ተጨማሪ ዓመት እንዲራዘምላቸው ተደርጎ የቆየ ሲሆን ያ የተራዘመው የአንድ ዓመት ጊዜ ደግሞ በቅርቡ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም መጠናቀቁን ተከተሎ ቦርዱ በድጋሚ ለአንድ ተጨማሪ ዓመት እንዲቀጥሉ ወስኗል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቢሾፍቱን አለም አቀፍ አየር መንገድን ጨምሮ በርካታ ግዙፍ የአቪዬሽን መሠረተ ልማትና የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ገቢራዊ እያደረገ ይገኛል።
በመሆኑም በእንዲህ ዓይነት ትልልቅ የዕድገት ምዕራፎች ወቅት የአመራር መረጋጋትና ቀጣይነት እንዲኖር ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ የዋና ሥራ አስፈጻሚው የአገልግሎት ጊዜ እንዲራዘም መደረጉ ተቋሙ የጀመራቸውን አበይት ሥራዎች በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ትልቅ መሠረት የሚጥል እርምጃ እንደሆነ ተገልጿል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.