የ6 ወር ህፃን ከፍርሽራሽ ስር በህይወት ተገኘች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኮሎምቢያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የ6 ወር ህፃን ከፍርሽራሽ ስር በተአምር በሕይወት ተገኘች።

በኮሎምቢያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ከአድካሚ ፍለጋና ጥረት በኋላ የ6 ህፃን እና እናቷን ከፍርስራሹ ስር በጥንቃቄ በማውጣት ህይወታቸውን ማዳን ተችሏል።

በኮሎምቢያ ከተከሰተው አስፈሪ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በስተጀርባ መላውን ዓለም ያስደነቀ ድንቅ ተአምር ተከስቷል።

ለሰዓታት በቆየውና እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት የህይወት አድን እርብርብ በፍርስራሹ ጥልቅ ስፍራ የተቀበሩትን ህፃኗንና እናቷን በህይወት ማውጣት ተችሏል።

የኮሎምቢያ መንግስት ይፋ ባደረገው የቅርብ ጊዜ መረጃ መሰረት የመሬት መንቀጥቀጡ እስካሁን የ132 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን 570 ያህል ሰዎች ደግሞ የተለያዩ አካላዊ ጉዳቶች ደርሶባቸዋል።

ምንም እንኳን አደጋው የፈጠረው ሀዘን እጅግ ከባድ ቢሆንም የዚች የ6 ወር ህፃንና የእናቷ በተአምር መተርፈ ግን ለሀገሪቱና ለዓለም ህዝብ ትልቅ ተስፋና መጽናኛ ሆኗል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Colombia
#earthquake
#emergency #magnitude


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1