ዶናልድ ትራምፕ ከኢራንን ስጋት ለማምለጥ በምግብ ማጓጓዣ መኪና እና በትንሽ አውሮፕላል ከቱርክ ወጡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቱርክ አንካራ ከተካሄደው የኔቶ ጉባኤ ማጠቃለያ በኋላ ከኢራን ኃይሎች የተሰነዘረባቸውን አደገኛ የግድያና የሮኬት ጥቃት ስጋት ለማምከን ሲባል በከፍተኛ ሚስጥር የተሞላ ለውጥ የአውሮፕላን አድርገዋል።

እንደ ዋሺንግተን ፖስት ዘገባ ከሆነ ትራምፕ በካሜራዎች ፊት ወደ ኤር ፎርስ ዋን አውሮፕላን የገቡ ቢሆንም ከጋዜጠኞችና ከተወሰኑ ሰራተኞች እይታ ውጭ በሆነው ሌላኛው የአውሮፕላኑ አቅጣጫ በተዘጋጀ የምግብ ማጓጓዣ የጭነት መኪና በመጠቀም ወደ ሌላ ትንሽ የC-32A ወታደራዊ አውሮፕላን በምስጢር ተዛውረዋል።

በዚህም ዋናው ኤር ፎርስ ዋን አውሮፕላን ጋዜጠኞችን አሳፍሮ እንደ ማታለያ ሆኖ እንዲበር የተደረገ ሲሆን በአሜሪካ ሴክሬት ሰርቪስ ስልት ፕሬዝዳንቱን የኢራንን የስጋት ቀጠና አልፈው በሰላም ወደ እንግሊዝ እንዲጓዙ አስችሏቸዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: