#Ethiopia | የዮርዳኖስ መንግሥት በፈረንጆች በ2030 የሚከበረውን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት 2000ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ለማክበር ዝግጅት ጀመረ።
የሀገሪቱ መንግሥት ለዝግጅቱ ብሔራዊ ኮሚቴ በማቋቋም የመጀመርያ ስብሰባውን አካሂዷል።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃፋር ሀሰን በመሩት በዚህ ስብሰባ ላይ የመንግሥት ሚኒስትሮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የቤተክርስቲያን መሪዎች ተገኝተዋል።
በዓሉ የዮርዳኖስን ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ስፍራዎች የሚያጎላ ከመሆኑም በላይ ሀገሪቱ ለዓለም አቀፍ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዋነኛ ማዕከል መሆኗን የሚያጠናክር እንደሆነ ተገልጿል።
ብሔራዊ ኮሚቴው በዮርዳኖስ ወንዝ ምስራቃዊ ዳርቻ በሚገኘውና “አል መግጣስ”በመባል በሚታወቀው ታሪካዊ የጥምቀት ስፍራ ዙሪያ መጠነ ሰፊ የልማት ሥራዎች ይከናወናሉ ብሏል።
ለአንግዶች እና ለመንፈሳዊ ተጓዦች የሚሆኑ ቤቶች፣የኢየሱስ ክርስቶስን ጥምቀት የሚያሳይ ሙዚየም ግንባታ የአረንጓዴ ኮሪደር ልማት እና የመሰረተ ልማት ማሻሻያዎች ይደረጋሉ ተብሏል።
ዮርዳኖስ ይህን ታሪካዊ ክስተት ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አብሮ የመኖር፣ የሰላም፣ የፍቅር እና በኃይማኖቶች መካከል ያለውን መከባበር ለማጉላት እንደምትጠቀምበት አስታውቃለች።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Jordan #religion
#Jesus #Believe
#baptism #John
#JafarHassan #KingAbdullah
Source: GetuTemesgen









No comments yet.