የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ይሰንዘራል በተባለ የደህንነት ስጋት ምክንያት ከቱርክ ወደ አሜሪካ ባደረጉት ጉዞ የምግብ ማጓጓዣ የጭነት መኪና (catering truck) በመጠቀም በምስጢር ወደ ሌላ አውሮፕላን መዛወራቸውን አስመልክቶ ከተጠየቁት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ስለ ሁኔታው ሲያስረዱ “ውሳኔው የሴክሬት ሰርቪስ (Secret Service) እና የጦር ኃይሉ የደህንነት አካላት ነው፤ በሌላ አውሮፕላን እና በተለየ በረራ እንድጓዝ ስለፈለጉ እኔ እነሱ ያሉኝን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ” ብለዋል።
በወቅቱ የደህንነት ስጋት (active threat) ስለመኖሩ ተጠይቀው ሲመልሱም፡ “ስጋት የነበረ ይመስለኛል፤ ሆኖም ዝርዝሩን አብዝቼ አልጠየቅኩም። ለእኔ ብዙ ጊዜ የተለያዩ ስጋቶችና ማስፈራሪያዎች ይደርሱኛል” ሲሉ ገልጸዋል።
ይህ አጋጣሚ የፕሬዝዳንቱን ደህንነት ለመጠበቅ የተወሰደ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሲሆን፣ የወጡት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከኢራን ወገን የተደቀነውን ስጋት ለማስቀረት የደህንነት አካላቱ ያልተለመደ የጉዞ መንገድ እንዲከተሉ አስገድዷቸዋል።
Source: Yeneta Tube









No comments yet.