🔴ነገ የሚካሄደውን የቦክስ ፌደዴሬሽን ጉባኤን ተከትሎ በሚኒስቴር መ/ቤቱና በኦሎምፒክ ኮሚቴ መካከል የከረረ አለመግባባት ተፈጥሯል
🔴”ጉባኤው መካሄድ ይችላል”ሚኒስቴር መ/ቤቱ
🔴”ማንኛውም ግለሠብ ወይም ፌዴሬሽን ነኝ የሚል አካል የጨረባ ምርጫ ላይ እንዳይሳተፍ”ኦሎምፒክ ኮሚቴ
🔴”ጉባኤውን አስተላልፋችሁ ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ”የዓለም ቦክስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ
#Ethiopia | ነገ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤን ተከትሎ በሚኒስቴር መ/ቤቱና በኦሎምፒክ ኮሚቴ መካከል የከረረ አለመግባባት ከወዲሁ መፈጠሩ ተሰምቷል።
የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ሀገራዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ነገ(ሐሙስ)ለማካሄድ ቀጠሮ ይዟል፤ይህንን ጉባኤ ህገ-ወጥ ነው፣በሀገር ላይ የተጣለውን ቅጣት ይበልጥ ያስቀጥላል በሚሉና ጉባኤውን አካሂዳለሁ ባለው የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን እንዲሁም ጉባኤውን ማካሄድ ትችላላችሁ ያለው ባህል ስፖርት በአንድ ወገን ጉባኤውን ማካሄድ አትችሉም፣ህገ-ወጥ ነው የሚለው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በሌላ ወገን የተካረረ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከደቂቃዎች በፊት በዋና ፀሐፊው አቶ ዳዊት አስፋው ፊርማና ማህተም ባወጣው መግለጫ “ሐገራችን ኢትዮጵያ ባሰፉት ዓመታት ከአህጉራዊና አለም አቀፋዊ የቦክስ ውድድሮች ተገልላ መቆየቷ ይታወቃል”በማለት ይጀምርና
ይህም የሆነው IBA በተባለው አለም አቀፍ ቦክሲንግ አሶሲዬሽን ሥር በኢትዮጵያዊ ግስሰብ የሚመራው ቦክሲንግ አሶሴዮሽን /ፌዴሬሽን/ በኢንተርናሽናል ኦሎምፒክ ኮሚቴ አውቅናው ስለተከለከለና በምትኩም በWBO /አለም አቀፍ ቦክሲንግ ኦርጋናይዜሽን/ አውቅና ተሰጥቶት ሀገራችንም ወደ WBO በጊዜ መግባት እና አባል ሆና መካተትና ጥቅሟን ማስከበር ሲገባት ግስሰቦች በፈጠሩት እንቅፋት ኢትዮጵያ በብዙ ስትቀጣ ቆይታለች፤ይሁንና የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለሁለት ዓመታት ባደረገው ክትትልና ሲፃፃፍ ቆይቶ አሁን እውቅና የምናገኝበትና ሙሉ አባል የምንሆንበት ደረጃ ላይ የምንደርስበት አድል እየተፈጠረ ይገኛል::
በዚህም መሰረት እንደ አዲስ ቦክሲንግ ፌዴሬሽን WBO-Ethiopia ተብሎ የሚቋቋም ሲሆን የሚያቋቋሙት ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ማለትም ሕጋዊነት የሚኖራቸው የጉባኤ አባላት ተሰብስበው በአለም ስቀፉ ቦክሲንግ ኦርጋናይዜሽን እና በዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ቻርተር መሰረት በሐገራችንን ሕግና ደንብ መሰረት በማድረግ ደንብ ወጥቶና ፀድቆ የምርጫ አስፈፃሚ ተሰይሞ በሚቋቋመው ቦክስ ፌዴሬሽን ላይ ባሉት የሐላፊነት ቦታዎች ላይ በሙሉ ማንኛውም በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ዕጩዎቻቸውን አቅርበው እንዲወዳደሩ በደንቡ መሰረት በቂ ጊዜ ተሰጥቷቸው ሲወዳደሩ ብቻ ነው”ካለ በኋላ መግለጫው ሲቀጥል
ይህንንም የሚያስፈፅሙት አዲስ ፌዴሬሽን እንደመሆኑ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የሚመርጧቸው የምርጫ አስፈፃሚዎች ብቻጰናቸው::
በተረፈ አውቅና የተከለከለውና እስካሁን ሀገሪቱ ቅጣት ሳይ እንድትቅይ ያደረጉት ግለሰብ አሁንም የሀገሪቱ አትሌቶች ዕድል እንዲጨናገፍና ችግሩም እንዲቀጥል የጨረባ ስብሰባና ምርጫ ካላካሄድኩ በማለት ጥሪ እያደረጉ መሆኑን በአሳቸው ከተገለሉ ተቋማት መረጃ ማግኘት ችለናል::
በመሆኑም የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴና የሚመለከተው አካል በጋራ በመሆን ሕጋዊ የሀገሪቱን ጥቅምና መብት በሚያስከብር ሁኔታ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሚጠቀሙበት የትኛውም ባለመብት ባልተገኘበት ሁኔታ ጉባኤ ማካሄድና ምርጫ ማስፈፀም እንዲያስችል በቅርቡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ የሚካሄድ ስለሆነ እስከዚያው ማንኛውም ግለሰብ ወይንም ፌዴሬሽን የሚል ነኝ የሚል አካል አለም አቀፍ ቦክሲንግ ኦርጋናይዜሽንን አስመልክቶ በሚያዘጋጀው ጉባኤ እና የጨረባ ምርጫ ላይ እንዳትሳተፉ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን::”ብሏል ጠንከር ያለው መግለጫ በመጨረሻ።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከላይ የቀረበውን ጠንከር ያለ መግለጫ ቢያወጣም ሚኒስቴር መ/ቤቱ በተለይ ክብርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ ጉባኤው መካሄድ ይችላል የሚል አቅጣጫ መስጠታቸውና ብሄራዊ ቦክስ ፌዴሬሽንም ሀገራዊ ጉባኤውን ለማካሄድ በመጨረሻ ሠዓት ላይ መገኘታቸው ነገሩን አወሳስቦት በቀጣይ የከፋ ችግር ወይም የተጣለውን ቅጣት እንዳያስቀጥለው የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዲፈጠር አድርጓል።
የሁለቱ አካላት አለመግባባት ያሳሰባቸው የዓለም ቦክስ ፌዴሬሽን ጄኔራል ሴክሬተሪ Tom Dielen በበኩላቸው “ጉባኤውን አስተላልፋችሁ፣ከኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር ገንቢ ውይይት አድርጋችሁ በመጪው ኦክቶበር ከሚደረገው የኤክስኪዩቲቭ ቦርድ ስብሠባ በፊት እንድታሳውቁን”በሚል የላኩት ደብዳቤ ከመከበር ይልቅ በመጣሱ ሀገሪቷን ለከፋ አደጋና የነበረው ቅጣት ተሻሽሎ ሊቀጥል ይቼላል የሚል ስጋት ከወዲሁ በብዙዎች እንዲፈጠር አድርጓል።
✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)


Source: GetuTemesgen








No comments yet.