#Ethiopia | ከዶናልድ ትራምፕ ጋር እሰጣገባ ውስጥ የገቡት የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ኢልሃን ኦማር በሜኔሶታ ግዛት 5ኛ ኮንግረስ ዲስትሪክት በተካሄደው የዴሞክራቲክ ፓርቲ የቅድመ ምርጫ ውድድር አብላጫ ድምፅ በማግኘት አሸናፊነታቸውን አረጋግጠዋል።
የሕዝብ ተወካይዋ ከጠቅላላው ድምፅ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን በከፍተኛ ብልጫ በማስመዝገብ ነበር ተፎካካሪዎቻቸውን በሰፊ ልዩነት ማሸነፍ የቻሉት።
ኢልሃን ኦማር ይህንን አመርቂ ድል የተቀዳጁት ከአሜሪካ-እስራኤል የሕዝብ ጉዳዮች ኮሚቴ (AIPAC) ምንም ዓይነት ድጋፍ ሳያገኙ መሆኑ ተገልጿል።
የኮንግረስ አባሏ ያስመዘገቡት ይህ የድምፅ ብልጫ በመራጮቻቸው ዘንድ ያላቸውን ጠንካራ ተቀባይነትና አመኔታ በግልጽ ያሳየ ሲሆን ወደሚቀጥለው አጠቃላይ ምርጫ በሙሉ ጥንካሬና በከፍተኛ ተስፋ እንዲሸጋገሩ ትልቅ መተማመንን ፈጥሮላቸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.