ከ10 ወጣቶች 9ኙ ዋስትና በሌላቸው ስራዎች ተቀጥረው ይሰራሉ ~ አይ.ኤል.ኦ

- Advertisement -
Sidebar AD

* የዓለም አቀፍ የወጣቶች ሥራ አጥነት ምጣኔ 12.4% ደርሷል

#Ethiopia | ይህም ወጣቶች ለሥራ አጥነት የመጋለጥ እድላቸው ከአዋቂዎች በ4 እጥፍ የላቀ መሆኑን ያሳያል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በ15 እና 24 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሥራ አጥ የሆኑ ወጣቶች ቁጥር 67 ሚሊዮን ደርሷል።

በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች በሥራ አጥነት እና የሥራ ዕድል እጥረት ፈተና ውስጥ እንደሚገኙ አስታወቀ።

ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚከበረው የወጣቶች ቀን የዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት (ILO) ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሠረት በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች በሥራ አጥነት እና በሥራ ዕድል እጥረት ፈተና ውስጥ እንደሚገኙ አስታውቋል።

ድርጅቱ ባወጣው መረጃ መሠረት በዓለም 257 ሚሊዮን ወይም 20 በመቶ የሚሆኑ ወጣቶች ከሥራና ከትምህርት የራቁ ናቸው ብሏል።

በታዳጊ አገራት በተለይም ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት ከ10 ወጣቶች መካከል 9ኙ መደበኛ ባልሆኑና ዋስትና በሌላቸው ጊዜያዊ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ አስታውቋል።

የዓለም ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ እና እየተካሄዱ የሚገኙ ጦርነቶች ወጣቶች የሥራ እድል እንዳያገኙ አድርጓል ሲል ድርጅቱ ገልጿል።

ቀጣሪዎች ከፍተኛ የሥራ ልምድ ያላቸው ሰዎች መፈለጋቸው ደግሞ አዲስ ተመረቂ ወጣቶችን ከሥራ ዓለም እንዲገለሉ አድርጓል ነው ያለው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#InternationalYouthDay
#ILO #NEET #InformalWork
#ExperienceParadox


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1