ኢትዮጵያዊው ሠዓሊ ሳምሶን መረሳ በስድስተኛው ዓለም አቀፍ ሚላን ቤሳራቢች የሥነጥበብ መድረክ የከበረ ሽልማት አበራ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከሃምሳ በላይ የዓለም አቀፍ ባለሙያዎች በተሳተፉበትና በዩጎዝላቪያ በተዘጋጀው ስድስተኛው ዓለም አቀፍ የሚላን ቤሳራቢች የሥነጥበብ ውድድር ላይ ኢትዮጵያዊው ሠዓሊ ሳምሶን መረሳ አሸናፊ በመሆን የሽልማቱ ባለቤት ሆኗል።

ሥነጥበብ ሕዝቦችን በማቀራረብ ረገድ የሚጫወተውን ሚና መሠረት በማድረግ ለሰው ልጅ ክብር፣ ለሰላምና ለአንድነት የቆሙ ሥራዎችን በሚያወዳድረው በዚህ መድረክ ሠዓሊው ሩትስ ተስፋ እና ዝምታ ከአውሎ ነፋስ በኋላ በተሰኙ ውብ የጥበብ ሥራዎቹ አሸንፏል።

በርካታ የዓለም አቀፍ እንግዶችና የዜና ማዕከላት በተገኙበት በዚሁ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ ሠዓሊ ሳምሶን ክብርን የሚያጎናጽፈውን ይህን ሽልማት ከሲልቨር ሌክ ቬሊኮ ግራዲሽቴ ማዘጋጃ ቤት ከንቲባ እጅ ተቀብሏል።

ሠዓሊው በሥራዎቹ ሰላም፣ ተስፋ፣ ሰብአዊነትና ጽናትን በጥበብ ያንጸባረቀ ሲሆን፣ የውድድሩ ዳኞችም የሰላም መነሻ የሰው ልጅ የውስጥ ማንነት መሆኑን በተፈጥሮ ምስሎች፣ በሕፃናትና በነጭ ርግብ አማካኝነት በጥበብ ገልጾ በማቅረቡ ለሽልማት እንደበቃ ገልጸዋል።

ሠዓሊ ሳምሶን መረሳ ሽልማቱን በተቀበለበት ወቅት ባደረገው ንግግር ጥበብ የውበት መግለጫ ብቻ ሳይሆን የሰላም ድምፅም እንደሆነች ጠቁሞ፣ ይህ ስኬት በተለይም ለሀገሩ ሕዝቦች ግጭትን ትተው በውይይትና በመግባባት መንገድ እንዲጓዙ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ የተመኘ መሆኑን ተናግሯል።

በፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ቱኒዚያ፣ አልጄሪያ፣ ግብፅ፣ ኳታር፣ ሱዳንና ሰርቢያ ሥራዎቹን በግልና በቡድን ኤግዚቢሽኖች ያቀረበው ሠዓሊ ሳምሶን መረሳ፣ በአፍሪካ የዘመናዊ ሥነጥበብ መድረክ ሀገሩን በክብር በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።

ይትባረክ ዋለልኝ

#ethiopianart #samsonmeressa #milanbesarabicaward #ethiopianartist #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: