#Ethiopia | አንጋፋው የፊልም ባለሙያ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በቅርቡ ባደረጉት የፖድካስት ቆይታ፣ አንዳንድ ሰዎች በስራ ውድቀት ወይም በህግ ጥያቄ ሲገጥሟቸው ስህተታቸውን አምኖ ከመቀበል ይልቅ «በብሔሬ ተጠቃሁ» እያሉ የዘር ካርድ እንደሚመዝዙ ተናገሩ።
በቂ እውቀትና የሞራል ጥንካሬ የሌላቸው እነዚህ ግለሰቦች፤ ከእውነት ለመሸሸግ እና የህዝብን ስሜት ለማሳሳት ሲሉ ብቻ የዘር ልዩነትን እንደ መከላከያ መሳሪያ ይጠቀሙበታል።
ህዝቡ መሬት ላይ የሚፈልገው ሰላም፣ ስራ እና የተረጋጋ ኑሮ ቢሆንም፣ እነዚህ ሰዎች ግን የራሳቸውን የግል ጥቅም ለማሳካት ሲሉ የህዝቡን ስም እየጠሩ ውንብድና ይሰራሉ።
ፕሮፌሰር ኃይሌ አክለውም፣ ዘረኝነት ለነዚህ ሰዎች የመጨረሻ መደበቂያ ቢሆንም፤ እውነተኛ ስኬትና ብርቱነት የሚለካው ግን የራሱን ስህተት አምኖ በመቀበል፣ በግል ተጠያቂነት በመመራት እና ከእውነት ጋር አብሮ በመኖር ብቻ መሆኑን አሳስበዋል።
Source: GetuTemesgen









No comments yet.