የሐሰተኛ መረጃን ለመግታትና የሚዲያ ቁጥጥሩን ለማዘመን ከተለያዩ ተቋማት የጋራ ስምምነት ተደረገ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ተለዋዋጭ የሆነውን የሚዲያ ዘርፍ አሠራር ለመምራትና የሀሰተኛ መረጃ ሥርጭትን በጋራ ለመግታት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራረመ።

‎ውጤታማና የዳበረ የሚዲያ ሬጉላቶሪ ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመውን ይህንን ስምምነት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀና የየተቋማቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች በጋራ አጽድቀውታል።

‎በትብብር መሥራት ላይ ያተኮረው ይህ ስምምነት የብሔራዊ ጥቅምንና የሕዝብ ደህንነትን ለማስጠበቅ፣ የጥላቻ ንግግሮችን ለመከላከል እንዲሁም የሳይበር ጥቃቶችን በጋራ ለመመከት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑ ተገልጿል።

‎​በስምምነቱ መሠረት ባለሥልጣኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ከማስተሳሰር ጀምሮ የባለቤትነት ዝውውር ሕጋዊነትን ማረጋገጥ፣ የመሣሪያዎች ፍተሻና የሚዲያ ቴክኖሎጂ ልማት ሥራዎች ከተባባሪዎቹ ተቋማት ጋር በቅንጅት ይከናወናሉ።

‎ስምምነቱን በይፋ ከፈረሙት መካከል የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ይገኙበታል።

‎ዋና ዳይሬክተሯ ኃይማኖት ዘለቀ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ በተናጠል የሚወሰድ የቁጥጥር እርምጃ ውጤታማ ባለመሆኑ ይህ አዲስ አሠራር የሕግ ማስፈጸም አቅምን ከማሳደጉም በላይ አገልግሎቶችን በአጭር ጊዜና በግልጽነት ለመስጠት ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።

‎​በዕለቱ በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አዝመራው አንደሞ በበኩላቸው፣ ነባሩ የመረጃ ነጻነት አዋጅ ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ትልቅ አስቻይ ሁኔታ መፍጠሩን አስታውሰው፣ አዲሱ ስምምነት ደግሞ የተቋማትን ቅንጅት በማጠናከር የሀገረ መንግሥት ግንባታውን ይበልጥ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

‎ባለሥልጣኑ ባለፉት ወራት ካከናወናቸው የሚዲያ ይዘት ክትትልና የ100 ቀናት ዕቅድ ግምገማዎች ጎን ለጎን፣ ተቋሙን ወደ ላቀ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ የሚያሻግር መሠረተ ልማት ለመዘርጋት ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁም አብሮ ገልጿል።

‎#Ethiopia #MediaRegulation #FakeNewsFree #DigitalMedia #EthiopianMedia #CyberSecurity #MediaLaw #FactChecking #CollaborativeGovernance







Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2