የጋብቻ ስርዓት ለፍቅራችን መለኪያ አይደለም!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ኦፕራ ዊንፍሬይ እናስቴድማን በአንድ ወቅት የታጩ ቢሆንም የጋብቻ ስርዓት ለፍቅራቸው መለኪያ ወይም ማሰሪያ ሊሆን እንደማይችል በመረዳት ሰርጉን ለመተው ወስነናል ሲሉ ተናግረው ነበር።

ኦፕራና እስቴድማን እውነተኛ የፍቅር አጋር ማለት ማንነትህን ሳይቀይር የራስህን ህልም እንድትኖር ነፃነት የሚሰጥህና መንገድህን የሚያበራልህ ነው ይላሉ።

በተለዋዋጭና አላፊ አግዳሚ በበዛበት በዚህ ዓለም እውነተኛ እና ዘላቂ የፍቅር ግንኙነት ማግኘት ብርቅ ሆኗል።

ጥንዶቹ የግንኙነታችሁን ጥንካሬና ስኬት የሚወስነው ማህበረሰቡ ባስቀመጠው ወግ ብቻ ሳይሆን የሁለታችሁም የውስጥ ስምምነትና ሰላም ነው የሚል አስተሳሰብ ያራምዳሉ።

ሆኖም ለየት ያለ የህይወት ፍልስፍናቸው አንዳቸው ለሌላቸው ባላቸው ጥልቅ እምነት እና መከባበር የኦፕራ ዊንፍሬይ እና የስቴድማን ግራሃም የ40 ዓመታት የፍቅር ጉዞ ዛሬም እውነት ሁኖ ቀጥሏል።

ከ1986 ዓ.ም. ጀምሮ አብረው የዘለቁት እነዚህ ጥንዶች እውነተኛ ፍቅር በእርግጥ ምን ማለት እንደሆነ በተግባር እያሳዩን ይገኛሉ።

የኦፕራ እና የስቴድማን ግንኙነት መሰረት ያደረገው የሌላኛውን ህልምና ስኬት ሳይጋርዱ አብሮ በመቆም ነው።

እንዲሁም አንዳቸው የሌላኛውን ማንነት ሳይጫኑ እና ሳይወስኑ በመደጋገፍ ላይ ነው።

ጥንዶቹ የግል ህይወታቸውን ከካሜራና ከህዝብ እይታ አርቀው በሚስጥር መጠበቅን ይመርጣሉ።

በቅርቡ በህዝብ ፊት አብረው በደስታ ሲታዩ ያሳዩት አወንታዊ ስሜት የሚያረጋግጠው እውነተኛ ፍቅር ለሰው ለማሳየት ሳይሆን ለራስ ህሊና እና ደስታ የሚኖር እንደሆነ ነው።

የኦፕራ እና የስቴድማን ጉዞ የሚያስታውሰን ፍቅርን የሚያጸናው የወርቅ ቀለበት ሳይሆን ዕለት ተዕለት የሚገነባ መተማመን ግልጽነት እና የማይናወጥ አጋርነት መሆኑን ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#OprahWinfrey #stedman
#Happiness #marriage
#Optimist


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: