#Ethiopia | በኢትዮጵያ በህክምና ሙያቸው ከ250 ሺህ በላይ ሰዎችን በማከም ረጅም እና ስኬታማ የሙያ ዘመንን ያሳለፉት ዶክተር ሰላማዊት አክሊሉ በህክምና አገልግሎት ውስጥ ከልብ የመነጨ ትኩረት፣ እውነተኛ አዳማጭነት እና ፍቅር የላቀ ዋጋ እንዳለው ከዶክተርስ ፕላስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።
ዶክተር ሰላማዊት ለወጣት የህክምና ባለሙያዎች ባካፈሉት አስተማሪ መልእክት፣ በህክምና ወቅት የሚደረግ የቃላት ልውውጥ የሚይዘው ድርሻ አነስተኛ እንደሆነና ዋናው ቁልፍ ከልብ የመነጨ የማዳመጥና ሰብአዊነትን የማስቀደድ ፍላጎት መሆኑን አስረድተዋል።
በታካሚ እና በሀኪም መካከል በሚደረግ ግንኙነት ውስጥ ታካሚው የሚረዳው እና በህሊናው የሚያስታውሰው የሀኪሙን ቅን ሀሳብ፣ ትስስር እና አቀራረብ መሆኑን ያመለከቱት ዶክተር ሰላማዊት የሰው ልጅ አካል ራሱን የማዳን አቅሙ የሚነቃቃው ባለሙያዎች በሙሉ ልብ ሲያዳምጡት እንደሆነ ገልጸዋል።
በመሆኑም ወጣት የህክምና ባለሙያዎች ስራቸውን ሲያከናውኑ የህመም ምልክቶችን ብቻ ከመመልከት ይልቅ በሙሉ ሰብአዊነት ለታካሚ ራስን በመስጠት “የበሽታ ሳይሆን የሰው ሀኪም” እንዲሆኑ አሳስበዋል።
አክለውም ወጣት ባለሙያዎች በሙያ ህይወታቸው መጨረሻ ላይ ወደኋላ ተመልሰው ሲያዩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከልባቸው ማገልገላቸውን በማሰብ የላቀ የህሊና እርካታ የሚያገኙበትን መንገድ አሁኑኑ መገንባት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.