#Eghiopia | በአንድ የፖላንድ ቢሊየነር ወጪው የተሸፈነው 182 ጫማ ቁመት ያለው የድንግል ማርያም ሐውልት ግንባታ ተጠናቆ በነሐሴ ወር መጨረሻ ለምረቃ እንደሚበቃ ተገለፀ።
ይህ ሐውልት በአውሮፓ አህጉር ትልቁና ረጅሙ የድንግል ማርያም ሐውልት ያደርገዋል።
የግንባታውን ወጪ ሙሉ በሙሉ የሸፈኑት ታዋቂው የፖላንድ ባለሀብት ሮማን ካርኮሲክ እና ባለቤታቸው ግራዚና መሆናቸው ታውቋል።
ፕሮጀክቱ ላለፉት አራት ዓመታት ሲያከናውኑ መቆየታቸው ነው የተገለፀው።
ይህ መንፈሳዊ ሀውልት በሀብትና በስልጣን ላይ ትኩረት በሚደረግበት በዚህ አለም ውስጥ የሰዎችን አእምሮ ወደ ላቀ መንፈሳዊ እሴትና እምነት የሚያነሳሳ አርማ እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Poland #spiritual
#statue #VirginMary
Source: GetuTemesgen









No comments yet.