የዶናልድ ትራምፕ የቅርብ ሰው የቅርጫት ኳስ ክለብ ሊገዙ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ታዋቂው የአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ክለብ ሎስ አንጀለስ ሌከርስ በ12.5 ቢሊዮን ዶላር በከፍተኛ ዋጋ ሊሸጥ ነው።

ታዋቂው የአሜሪካ ኤን.ቢ.ኤ ቅርጫት ኳስ ክለብ ሎስ አንጀለስ ሌከርስ በታሪክ ከፍተኛ በሆነ 12.5 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ለሁለት አሜሪካውያን ባለሀብቶች ሊሸጥ መስማማቱ ተገለጸ።

የቅርጫች ኳስ ክክለቡን የሚገዙት
የቀድሞው የዲዝኒ ዋልት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቦብ አይገርና የዶናልድ ትራምፕ አማች ወንድም የሆነው የቬንቸር ካፒታል ባለቤቱ ጆሽ ኩሽነር መሆናቸው ታውቋል።

አይገር እና ኩሽነር ቀደም ሲል በላስ ቬጋስ አዲስ የኤን.ቢ.ኤ ክለብ የማቋቋም እቅድ የነበራቸው ቢሆንም ሃሳባቸውን በመቀየር ሎስ አንጀለስ ሌከርስን ለመግዛት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የቅርጫት ኳስ ክለቡ ባለቤት የነበሩት ማርክ ዋልተር በ2025 ነበር በ10 ቢሊዮን ዶላር የግላቸው አድርገውት የነበረው።

አሁን ከአንድ አመት በኋላ 2.5 ቢሊዮን ዶላር በማትረፍ የቅርጫት ኳስ ክለቡን አሳልፈው ልሰጡ ከጫፍ ደርሰዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Usa #NBA #LALakers
#JoshKushner #BobIger
#BBCsports #Fans


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2