በአሜሪካ ስማቸውን የገነነው ኢትዮጵያዊው የሒሳብ ሊቅ ፕሮፌሰር ሙላቱ ለማ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ኢትዮጵያዊው የሒሳብ ሊቅና ፕሮፌሰር ሙላቱ ለማ በሒሳብ ትምህርት በምርምር እንዲሁም ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች በመኮትኮት ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ስም ማተርፋቸው ታሪክ ሰናጁ ጀማል አብዱላዚዝ ዘግቧል።

የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቁት ፕሮፌሰር ሙላቱ የዶክትሬት (Ph.D.) ዲግሪያቸውን ከአሜሪካው ‘Kent State University’ ካገኙ በኋላ በአሜሪካ ጆርጂያ በሚገኘው ‘Savannah State University’ በፕሮፌሰርነትና በምርምር ዘርፍ ለበርካታ አስርት ዓመታት በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

​ፕሮፌሰር ሙላቱ በሒሳብ ምርምር ዘርፍ በተለይም በ’Number Theory’ እና ‘Fibonacci Numbers’ ዙሪያ ባደረጓቸው ጥናቶች አዳዲስ የሒሳብ ቀመሮችንና ንድፈ-ሃሳቦችን ያፈለቁ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2011 በስማቸው የተሰየመውን “የሙላቱ ቁጥር” የተሰኘ የሒሳብ ቀመር ለዓለም አስተዋውቀዋል።

ከምርምር ሥራዎቻቸው በተጨማሪ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙና ተስፋ ያላቸውን ተማሪዎች በሒሳብ ትምህርት በማብቃት ረገድ ባሳዩት የላቀ መሪነት ከኋይት ሐውስ የሚሰጠውን ታላቅ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የሳይንስ፣ ሒሳብና ምህንድስና የማማከር አቀራረብ (Mentoring) ሽልማትን ጨምሮ የበርካታ የዩኒቨርሲቲዎችና የሳይንስ ማህበራት የዓመቱ መምህርና ተመራማሪ ሽልማቶችን መጎናጸፍ ችለዋል።

(ከስር የተያያዘው ምስል ”የሙላቱ ቁጥር” የተሰኘው የፕሮፌሰር ሙላቱ ለማ የሒሳብ ቀመር ነው )

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: