አቶ ነቢዩ የተባሉት የአሜሪካ ነዋሪ በስለት ጥቃት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስል ዋሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በአሜሪካ ሞንትጎመሪ ካውንቲ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ ሳቢያ ከሌላኛው አሽከርካሪ ጋር በተፈጠረ አምባጓሮ በስለት ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉት የ55 ዓመቱ የታኮማ ፓርክ ነዋሪ አቶ ነቢዩ ተክሉ ገብረሚካኤል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

እንደ ፖሊስ መግለጫ ከሆነ አደጋው በሁስተን ኤቭንዩ እና በሮአኖክ ኤቭንዩ አቅራቢያ የተከሰተ ሲሆን ሁለቱ ተሽከርካሪዎች ከተጋጩ በኋላ ነቢዩ ተክሉ ስለታም መሳሪያ በመጠቀም በሌላኛው አሽከርካሪ ላይ ከባድ ጥቃት አድርሰዋል።

​በጥቃቱ ሳቢያ በጽኑ የተጎዳው የ47 ዓመቱ አሽከርካሪ በወቅቱ በአስቸኳይ ወደ ህክምና ማዕከል ተወስዶ ድገተኛ ቀዶ ሕክምና ከተደረገለት በኋላ ወደ ሙሉ ጤናው ተመልሷል።

ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ከአካባቢው ሰወር ብለው የከረሙት አቶ ነብዩ ከሶስት ቀናት በፊት ወደ መኖሪያ ቤታቸው መመለሳቸውን መርማሪዎች ባገኙት ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

​በአሁኑ ወቅት አቶ ነቢዩ ተክሉ ወደ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ማዕከላዊ የምርመራ ጣቢያ የተወሰዱ ሲሆን በአንደኛ ደረጃ ግድያ በአንደኛና በሁለተኛ ደረጃ ከባድ ጥቃት ማድረስ እንዲሁም ሰዎችን አደጋ ላይ መጣል በሚሉ ተደራራቢ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2