#Ethiopia | ለጊዜው ስለተከበረው ገጣሚና ፀሐፊ በእውቀቱ ስዩም ማውራቴን ለሌላ ጊዜ ላቆየውና፤ ዛሬ ግን ስለ አንድ ሰው የሚሰማኝን ልናገር፤ ስለ ያሬድ ሹመቴ።
ያሬድ ሹመቴን ሳስበው ከሁሉ በፊት የሚመጣልኝ ጥያቄ፡ “እንዴት አይለወጥም?” የሚለው ነው።
ዘመን ተለወጠ፤ ሁኔታዎች ተቀየሩ የሰዎች አቋም ከአንድ ጎን ወደ ሌላ ተንሸራተተ፤ እሱ ግን ከሚያምንበት መርህ ሳይወጣ ራሱን ጠብቆ ቆይቷል።
ይህ ማለት ሰው ፈጽሞ አይለወጥ ማለት አይደለም።
ለእኔ ያሬድ ሹመቴ የሚያስደንቀኝ የሚቀየረውንና የማይቀየረውን መለየቱ ነው።
ዘመኑን ይከተላል፤ መርሁን ግን አይሸጥም። ወደፊት ይመለከታል፤ ያለፈውን ግን አይረሳም።
ከዚህ በላይ ደግሞ ሀገሩንና ህዝቡን መውደድ በቃላት ብቻ የሚገለጽ ነገር እንዳልሆነ በአቋሙ የሚያሳይ ሰው ይመስለኛል።
የጭቆና ባህሪ ከየትኛውም አቅጣጫ ቢመጣ መቃወም፤ ለሰው ልጅ ክብር መቆምና ትናንትን ሳይክድ ነገን መመልከት እነዚህ ነገሮች በእሱ ስብዕና ውስጥ የሚታዩ መስመሮች ናቸው።
በዚህ ዘመን አቋም መያዝ ከባድ ነው።
የሰዎች አድናቆት ሲያስፈልግህ አቋምህን መጠበቅ፤ ትችት ሲመጣብህ እንዳትሸሽ፤ የዘመኑ ነፋስ በሚነፍስበት አቅጣጫ ሁሉ እንዳትነጠልጣል።
ይህ ቀላል ነገር አይደለም።
ለዚህም ነው ያሬድ ሹመቴን ከስራው በላይ እንደ ስብዕና የማደንቀው።
ምክንያቱም ሰው ምን እንደሚሰራ ብቻ ሳይሆን፤ ለምን እንደሚሰራና በምን መርህ እንደሚኖርም ይገልጻል።
እኔ የማደንቀው ያሬድ ሹመቴ በሰው የተገነባ ሰው ሳይሆን፤ በአቋሙ ራሱን የገነባ ሰው መሆኑን ነው።
እናንተስ ያሬድ ሹመቴን እንዴት ታዩታላችሁ?
ከስራው ከአቋሙ ወይም ከስብዕናው የሚያስደንቃችሁ ምንድነው?
ሀሳባችሁን ከተሞክሯችሁ ጋር አያይዛችሁ ፃፉልኝ።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
Source: GetuTemesgen









No comments yet.