መንትያ ሴት ልጆቹን ከሞት ለመታደግ ፊትና ሰውነቱ በእሳት የተቃጠሉበት አባት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር 2021 ሬይ ሉቃስ የመኖሪያ ቤቱ በከፍተኛ እሳት ሲያያዝ ገና የ18 ወር ዕድሜ ያላቸው መንትያ ሴት ልጆቹ ማሌዥያ እና ሚላን በቃጠሎው መካከለኛ ክፍል ውስጥ ተከበው ቀሩ።

ሬይ ስለሚደርስበት አደጋ ሳያወላውል እና የራሱን ሕይወት ሳይስስት የልጆቹን ሕይወት ለማዳን ቀጥታ ወደሚንቀለቀለው እሳት ውስጥ ዘልቆ ገባ።

​በዚህ ድፍረት በተሞላበት እርምጃው ልጆቹን በሕይወት ማውጣት ቢችልም በእርሱ ላይ ግን ከባድ የሰውነት መቃጠል አደጋ እና በጊዜያዊነት የማየት አቅምን ማጣት አጋጥሞታል።

መኖሪያ ቤታቸው በእሳት ​ከወደመ በኋላ ሬይ እና ቤተሰቡ ሕይወታቸውን እንደገና ለመገንባት በተገደዱበት ወቅት የአካባቢው ማህበረሰብ ከጎናቸው በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ አድርጎላቸዋል።

አባት ለልጆቹ ሲል ሕይወቱን አደጋ ላይ ሲጥል ማህበረሰቡ ደግሞ ለዚህ አባት እጁን በመዘርጋት በብዙ ድጋፍ ጭምር አብረውት ሆነዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: