በግሌ ሀፍረት ተሰምቶኛል” – ራማፎዛ
#Ethiopia | የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ባሉ አንዳንድ የውጭ ዜጎች አያያዝ ላይ በደረሰው ጥቃት ሀፍረት እንደተሰማቸው ገለጹ።
ይህን ያሉት ሰዎች በኃይል እና በዛቻ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የተገደዱባቸውን ሪፖርቶች ከመረመሩ በኋላ ነው ተብሏል።
በዛሬው እለት በደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ሲሪል ራማፎሳ በውጭ ዜጎች ላይ የሚሰነዘረውን የጥላቻ ጥቃት አጥብቀው አውግዘዋል።
ይህ ቀውስ ደቡብ አፍሪካ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን መልካም ግንኙነት እየጎዳው መሆኑን በግልጽ አምነዋል።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ይህ ድርጊት በአፍሪካውያን ስደተኞች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት እና የሀገሪቱን ስም በመላው አለም እያጎደፈው መሆኑን በይፋ ተቀብለዋል።
በሃገር ውስጥ በርካታ የማያግባቡን ጉዳዮች ቢኖሩም ሌሎች አፍሪካውያን ወንድም እና እህቶችን የጥቃት ኢላማ ማድረግ ምክንያት ሊሆን አይገባም ብለዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Southafrica #Xenophobia
#SADC #Diplomacy
Source: GetuTemesgen









No comments yet.