በኢትዮጵያ ጥምር ዜግነት እንዳይፈቀድ ስምምነት ለይ ተደረሰ የግል መገናኛ ብዙኋን በገለልተኛ ቦርድ እንዲተዳደሩ ስምምነት ላይ …

- Advertisement -
Sidebar AD
በኢትዮጵያ ጥምር ዜግነት እንዳይፈቀድ ስምምነት ለይ ተደረሰ
የግል መገናኛ ብዙኋን በገለልተኛ ቦርድ እንዲተዳደሩ ስምምነት ላይ ተደርሷል ተብሏል
በኢትዮጵያ ጥምር ዜግነት ለጊዜው እንዳይፈቀድ፣ ወደፊት ግን የአገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ እየታየ ውሳኔ እንዲሰጥበት፣ የተቋማት ግንባታ፤ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች አጃንዳ ላይ የ500  ቡድን ተመካካሪዎች መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ።
የፖለቲካ ፓርቲዎችን ወክለው በዚህ አጀንዳ ላይ ተወያይ የሆኑት የቁጫ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ተወካይ አቶ ዓለማየሁ እኩሌ፣ በዚህ አጀንዳ በቀረቡ 109 ምክረሐሳቦች ላይ ተመካካሪዎች ከመግባባት መድረሳቸውን፣ ሐሳብ በልዩነት፣ ባለመግባባት ወደ ቅርቃርና ወደ አስታራቂ ሽማግሌ አለመግባቱን ለሪፖርተር ገልጸዋል።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን (ዳያስፖራ) ጉዳይ፣ የጥምር ዜግነት መብት እውቅናና ሌሎች ጉዳዮች፣ በንዑስ አጀንዳነት የቀረቡ ሲሆን፤ የጣምራ ዜግነት፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት ኢትዮጵያ አሁን ከደረሰችበት ዕድገት ደረጃ አኳያ ሙሉ ለሙሉ ከተሰጠ ለአገር ሉዓላዊነት አዳጋች እንደሚሆንና ወንጀል ሊያስፋፋ ስለሚችል ለጊዜው ሳይፈቀድ እንዲቆይ፣ ሆኖም ወደፊት ግን ተጨባጭ ሁኔታዎች እየታዩ የሚፈቀድበት ሁኔታ እንዲኖር የሚያስችለው ምህዳሩ ክፍት እንዲሆን በምክረሐሳብ ደረጃ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።
ጣምራ ዜግነት ይሰጥ ከተባለ እንደ ግብፅ፣ ኤርትራና ሱዳን ያሉ አገሮች ውስጥ የሚገኙ ዜጎች መብት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው። ይህ ደግሞ የአገርን ሚስጥር አሳልፎ ለመስጠት መፍቀድ ስለሚሆን ለጊዜው መሰጠት የለበትም።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1