በፍቅር ግንኙነት ውስጥ በፍፁም ቸል ሊባሉ የማይገቡ 10 የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ​አንዳንድ ጊዜ የፍቅር ግንኙነቶች ሲጀምሩ እጅ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በፍቅር ግንኙነት ውስጥ በፍፁም ቸል ሊባሉ የማይገቡ 10 የማስጠንቀቂያ ምልክቶች
​አንዳንድ ጊዜ የፍቅር ግንኙነቶች ሲጀምሩ እጅግ ማራኪና ፍጹም ይመስላሉ፤ ነገር ግን ጊዜ እያለፈ ሲሄድ አደገኛና መርዛማ ባህሪያት መታየት ይጀምራሉ። እነዚህን የጉዳት ምልክቶች  በፍቅር፣ በስሜት ወይም “ሰውየው ከጊዜ በኋላ ይለወጣል” በሚል ተስፋ ሸፍኖ ማለፍ ለከፍተኛ ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ይዳርጋል።
​አንድ ግንኙነት ጤናማ አለመሆኑን የሚያሳዩ 10 አደገኛ ምልክቶች፦
🔹 1. ቃላትና ድርጊት አለመጣጣም
ተጣማሪዎ የሚናገረውና የሚያደርገው ነገር የማይገናኝ ከሆነ ትልቅ ምልክት ነው። ሁልጊዜ የተለየ ነገር ቃል እየገባ የተለየ ተግባር የሚያከናውን ከሆነ፣ ከቃላቱ ይልቅ ድርጊቱን እመኑ።
🔹 2. ቃላትን መምረጥና በፍርሃት መኖር
ከባልደረባዎ ጋር በሚነጋገሩበት ወቅት ጭቅጭቅ፣ ቁጣ ወይም ስድብ እንዳይነሳ በማሰብ ብቻ እያንዳንዱን ቃላችሁን ተጠንቅቃችሁ የምትናገሩ ከሆነ ግንኙነቱ ጤናማ አይደለም። በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት ሊኖር ይገባል።
🔹 3. የቅርብ ሰዎችና የቤተሰብ ስጋት
ቤተሰቦቻችሁ ወይም የቅርብ ጓደኞቻችሁ በእናንተ ላይ ለውጥ ካዩ ወይም የባልደረባችሁን አደገኛ ባህሪ አስተውለው ካስጠነቀቋችሁ ሀሳባቸውን ቸል አትበሉ። በተለይ ባልደረባችሁ “እኛን ለማላቀቅ ነው የሚፈልጉት” በማለት ከወዳጆቻችሁ ሊያርቃችሁ ሲሞክር ተጠንቀቁ።
🔹 4. ወሰን ያለፈ ቅናትና ቁጥጥር
ከሌሎች ሰዎች ጋር በመገናኘታችሁ የሚቆጣ፣ ከማን ጋር መነጋገር እንዳለባችሁ የሚወስንና ሁልጊዜ የት እንዳላችሁ የሚቆጣጠር ከሆነ ይህ የባለቤትነትና የቁጥጥር ስሜት ማሳያ እንጂ የፍቅር ምልክት አይደለም።
🔹 5. የሚወዷቸውን ነገሮች ማቆም
የምትወዱትን ስፖርት፣ የትርፍ ጊዜ ማለፊያ (Hobbies)፣ ወይም ማህበራዊ ህይወታችሁን እንድታቆሙ የሚያስገድዳችሁ ከሆነ ግንኙነቱን ድጋሚ መመርመር ያስፈልጋል። ጤናማ ፍቅር የራሳችሁን ህይወት እንድታጡ አያደርግም።
🔹 6. ደስታችሁንና ፍላጎታችሁን መቀነስ
የሚያስደስቷችሁን ነገሮች፣ አላማዎቻችሁን ወይም መዝናኛዎቻችሁን የሚያሳንስና የሚያፌዝበት ከሆነ ይህ የእንክብካቤና የክብር መጎደልን ያሳያል። የማያቋርጥ ንቀትና ማሳነስ በ”ቀልድ” ስም ሊሸፈን አይገባም።
🔹 7. ሁሉንም ነገር ወደ እሱ/እሷ ብቻ ማዞር
ማንኛውም ውይይት ሁልጊዜ ስለ ባልደረባችሁ ችግር፣ ፍላጎትና ስሜት ብቻ የሚያልፍ ከሆነ እና ለእናተ ሀሳብና ስሜት ቦታ ከሌለ ግንኙነቱ ሚዛናዊ አይደለም። ጤናማ ግንኙነት የሁለቱንም ወገን አዳምጭነት ይጠይቃል።
🔹 8. ብቻችሁን እንድትንቀሳቀሱ አለመፍቀድ
ከቤተሰብና ከጓደኛ ጋር የሚኖራችሁን ግንኙነት በማቀብ ብቻችሁን እንድትሆኑ የሚያደርግ ሰው፣ ከጊዜ በኋላ ከመርዳት ይልቅ ለብቻችሁ ነጥሎ ጉዳት ለማድረስ ሊያመቻቻችሁ ይችላል። ሁለታችሁም የየራሳችሁ ወዳጆችና ጊዜ ሊኖራችሁ ይገባል።
🔹 9. ጥፋትን/ስህተትን በፍፁም አለመቀበል
ለሚያደርገው መጥፎ ድርጊት ሁልጊዜ እናንተን የሚወቅስና ሃላፊነት የማይወስድ ከሆነ ትልቅ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው። እንዲያውም እናንተን በስሜታዊነት፣ በራስ ወዳድነት ወይም የችግሩ መንስኤ አድርጎ ለማሳየት ይሞክራል።
🔹 10. ለግቦቻችሁ ድጋፍ አለመስጠት
ትክክለኛ አጋር ወደፊት እንድትራመዱ የሚያበረታታ እንጂ ወደኋላ የሚጎትት አይደለም። ትልሞችህንና ግቦችህን የሚቃወም ወይም ድጋፍ የማይሰጥ ከሆነ ይህንን ምልክት ችላ ልትሉት አይገባም።

👉ወደ ፍቅር ግንኙነት ከመግባትዎ በፊት ማን እንደሆኑ፣ ምን እንደሚያስፈልግዎትና የእርስዎን እሴቶች በደንብ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ፍቅር ማለት የራስን ማንነትና ደስታ አጥቶ መኖር ማለት አይደለም።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1