#Ethiopia | ናይጄሪያዊው ጋዜጠኛ ዳቪድ ሁንደይን አዲሱ የአሜሪካ ሕግ ሙሰኛ የአፍሪካ መሪዎች ሀብታቸውን በአሜሪካ እንዲደብቁ መንገድ ይከፍታል» ሲል አስጠነቀቀ።
ጋዜጠኛው አሜሪካ የኩባንያዎችን እውነተኛ ባለቤት የማሳወቅ ግዴታን ለመሻር የወሰደችውን እርምጃ አጥብቆ ነቅፏል።
በአዲሱ ደንብ መሠረት የአሜሪካ ኩባንያዎችና ዜጎች የኩባንያዎቻቸውን እውነተኛ ባለቤቶች ማንነት ለፋይናንስ ወንጀሎች መቆጣጠርያ ተቋም የማሳወቅ ግዴታ አይኖርባቸውም ይላል።
የአሜሪካ መንግሥት ቀደም ሲል በአሜሪካ ኩባንያዎችና ዜጎች ተመዝግበው በቋቱ ውስጥ የነበሩትን የባለቤትነት መረጃዎች ሙሉ በሙሉ እንደሚሰርዝ አስታውቋል።
አዲሱ ህግ ሙሰኞች ስማቸውን ሳይጠቅሱ በሌሎች ሰዎች ወይም በስም ብቻ በሚቋቋሙ ኩባንያዎች አማካይነት የዘረፉትን ገንዘብ ወደ አሜሪካ እንዲያስገቡ መንገዱን ይጠርግላቸዋል ሲል ጋዜጠኛው ሞግቷል።
ይህ አሰራር ግልጽነትን የሚያጠፋና ከታዳጊ ሀገራት በሙስና የተዘረፈ ሀብት በምስጢራዊ ኩባንያዎች አማካይነት ወደ አሜሪካ የፋይናንስ ስርዓት እንዳይገባ የሚከለክለውን ቁጥጥር የሚያዳክም መሆኑ ጋዜጠኛው ገልጿል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#USA #Nigeria #journalist
#BeneficialOwner #Database
#ShellCompanies
Source: GetuTemesgen









No comments yet.