የጻድቁ አባታችን አቡነ ኪሮስ ረድኤት እና ምልጃ አይለየን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ጻድቁ አባት አባ ኪሮስ ከመባሉ በፊት ስሙ “ዲላሶር” ይባል ነበር፡፡ ታኅሣሥ 8 ቀን ከነገስታት ወገን ተወለደ፡፡ አባቱ ሲሞት ከታላቅ ወንድሙ ጋር ሀብቱን በመካፈል ለድሆች መጸወተ፡፡ ወደ ሀገረ ሮም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሲሄድም ከአንዲት በዓት የራስ ፀጉሩ እስከ እግሩ የሚደርስ፣ አባ በብኑዳ የሚባል ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ወጥቶ “ኪሮስ መነኲሴ ለመሆን ወደዚህ መጣህን? አለው፡፡ ኪሮስም ቀርቦ ተባረከና ሦስት ቀን ከቆየ በኋላ ደግሞ ጠየቀው፡፡ እርሱም “አዎ በጣም እፈልጋለሁ” አለው፡፡ አባ በብኑዳም ትንሽ ደመናን ጠርቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም በመሄድ የምንኲስናን ልብስ አምጥቶ አለበሰው፡፡ ለአባ በብኑዳ ሁልጊዜ በሠርክ ሰማያዊ ኅብስትና ወይን ቅዱስ ሚካኤል ያመጣለት ነበር፡፡ አባ ኪሮስ እየታዘዘው ሲኖር፣ አንድ ቅንነት የሌለው መነኩሴ ወደ አባ በብኑዳ መጣ፡፡

የሠርክ ጸሎት ሲጸልዩም ቅዱስ ሚካኤል የተዘጋጀ ኅብስትና ወይን ለአባ በብኑዳ ሰጠው፡፡ እንግዳውም ሲመገቡ ከዚያ ኅብስተ ሰማይ ደብቆ ወደ አስቄጥስ ገዳም በመውሰድ ለመነኰሳቱ እያሳየ ሲያወራላቸው ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ሕብስቷን ነጥቆ ወሰዳት፡፡ የአስቄጥስ ገዳም ቅዱሳንም ያን መነኲሴ “እኛን ማን መምህርና ፈራጅ አድርጐ ሾመን” አሉት፡፡ እግዚአብሔርም “የተቀደሰውን ለውሻ በመስጠቱ በአባ በብኑዳ አዘነበት በአንበሳም ተሰብሮ ሞተ፡፡ ኅብስቱም በበረሃ ላለ ፊልሞና ለሚባል መነኲሴ እስከ ዕለተ ሞቱ ምግብ እንዲሆነው ተሰጠው፡፡ አባ ኪሮስም መምህሩ ስለሞተበት አርባ ዓመት መሬት ላይ ተጣብቆ ሲጸልይ ግማሽ ሥጋው አለቀ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስነስቶ መላ ሰውነቱን ዳበሰው፤ ሰውነቱ እንደ ሕፃን ሆነ፡፡

በምድር ላይ ሰግዶ ጌታችን እንደ መብረቅ ሲለወጥና እልፍ አእላፋት መላእክት ሲያመሰግኑት አያቸው፡፡ ጌታችንም “ኪሮስ ሆይ በምድር ላይ እንዳንተ ትዕግሥትን የለበሰ አላገኘሁም አለው፡፡ የአባ በብኑዳ ነፍስም በቅድስና አርፋለች አለው፡፡ ኪሮስም “ጌታዬ ሆይ ፍርድህ ቅን ነው” አለ፡፡ ከዚህ በኋላም ቅዱስ አባ ኪሮስ በገድልና በትሩፋት እየተቀጠቀጠ ከኖረ በኋላ በ270 ዓመቱ ሐምሌ 8 ቀን አርፏል፡፡ ጌታችንም መውለድ የተሳናቸው ሴቶች በስሙ ለምነው ፍሬ እንደሚያገኙ የዘከረውም በበረከት እንደሚሞላ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ ገዳማውያን ጌታችን ምላሽ እስኪሰጣቸው ጸንተው ይጸልያሉ፡፡ በረከታቸው እንዲያድርብን ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጸና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1