“የሜክሲኮ የነፍስ አድን ቡድን አልቀበልም!” – ኮሎምቢያ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከሜክሲኮ የተላከውን የወታደራዊና የነፍስ አድን ቡድን የኮሎምቢያ መንግስት አልቀበልም ማለቱን የሜክሲኮ ፕሬዚዳንት ክላውዲያ ሼይንባውም ገልጸዋል።

የነፍስ አድን ቡድኑ በርካታ አለም አቀፍ የምስክር ወረቀቶች ያሉት እና በ98 ሀገራት አደጋዎችን በመታደግ ልምድ ያለው ቢሆንም የኮሎምቢያ ባለስልጣናት ተጨማሪ ማረጋገጫ በሚል ቡድኑ ወደ ስራ መግባት ሳይችል ቀርቷል ብለዋል

ኮሎምቢያ በበኩሏ የፍለጋ እና የነፍስ አድን ስራው ጥብቅ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ሀገራትን ቡድኖች ብቻ የሚያሳትፍ በመሆኑ ነው ብላለች።

በፍለጋ ስራው እንደ አሜሪካ ኤል ሳልቫዶር ኢኳዶር እና እስራኤል ካሉ ሀገራት የተላኩ ቡድኖች ስራውን እያከናወኑ ይገኛል ተብሏል።

በኮሎምቢያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ270 በላይ ደርሷል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም የገቡበት ባለመታወቁ በፍርስራሾች ስር በህይወት ያሉ ሰዎችን የመፈለጉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ሜክሲኮ ምንም እንኳ የነፍስ አድን ቡድኗ ፈቃድ ባያገኝም በሄርኩሌስ የጦር አውሮፕላኖቿ አማካኝነት ከ58 ቶን በላይ ምግብ የመድኃኒት እና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ወደ ኮሎምቢያ መላኳን አረጋግጣለች።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Colombia #Mexico
#Earthquake #Support
#INSARAG #rescueteam


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1