#Ethiopia | ዩጋንዳ ዋና ከተማዋን ካምፓላ ቀስ በቀስ ወደ ናካሶንጎላ ለማዛወር የሚያስችላትን ሰፊ ዕቅድ ይፋ አድርጋለች።
ይህ የከተማ ዝውውር ፕሮጀክት እስከ ፈረንጆቹ 2040 ድረስ ሊራዘም እንደሚችል ተገልጿል።
የዩጋንዳ የከተማ ልማት ሚኒስትር ማርጋሬት ሙሃንጋ እንዳስታወቁት የውሳኔው ዋነኛ ምክንያት የካምፓላ ከተማ አሰልቺ የሆነ የትራፊክና የሕዝብ መጨናነቅ እንዲሁም ደካማ የከተማ አደረጃጀትና ዕቅድ በመሆኑ ነው ብለዋል።
ናካሶንጎላ ከተማ ለዘመናዊና የታቀደ አዲስ ዋና ከተማ ግንባታ የሚሆን ሰፊና ምቹ መሬት ያላት በመሆኑ ለዚህ ትልቅ ፕሮጀክት መመረጧን ገልፀዋል።
የዝውውር ሂደቱ በአንድ ጊዜ ሳይሆን ቀስ በቀስ የሚከናወን ይሆናል።
በዝግጅቱ መሠረት የተወሰኑ የመንግሥት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች አስቀድመው ወደ አዲሷ ከተማ የሚዛወሩ ይሆናል ብለዋል።
ይህ ፕሮጀክት ከተተገበረ ከአፍሪካ ትልልቅ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Uganda #Kampala
#Vision2040
#planning
Source: GetuTemesgen








No comments yet.