ባንዳ ለሆዱ ሲሞት እኛ ለሀገር ሉዓላዊነት ለህዝቦች ክብርና አንድነት እንሞታለን-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላሻዕቢያ ከጅምሩ ኢትዮ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ባንዳ ለሆዱ ሲሞት እኛ ለሀገር ሉዓላዊነት ለህዝቦች ክብርና አንድነት እንሞታለን-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ‼️
ሻዕቢያ ከጅምሩ ኢትዮጵያን ከባህር በር ለማራቅ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ፅምዶ ፈጥሮ ኢትዮጵያ ላይ ደባ የሰራ ሃይል ነው  ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ህወሃትም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ የሸጠና ለ27 አመታት ስልጣን ይዞ ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታጣ አጠንክሮ የሰራ ቅጥረኛ የገዛ አገሩን ሠራዊት ያጠቃ የክህደት ሃይል ነው ብለዋል ። ኢትዮጵያ  በተደጋጋሚ በሕወሃት ክህደት የተፈተነች ነገር ግን ፀንታ የቆመች የልዩ ዘመቻ ሠራዊት መሰል ጠንካራ አርበኛ ልጆች ያሏት አገር ስለሆነች ጉዞዋን ቀጥላለች ብለዋል።
የጥፋት ሃይሎች በባዕዳን ስትራቴጂ ሥር ተሰልፈው ኢትዮጵያን የማዳከምና የማፍረስ ፅምዶ የተባለ ጥምረት ቀርፀው ሕዝባችንን ለስቃይና መከራ በመዳረግ ደካማ ኢትዮጵያን ለማየት ጓጉተው ቢሠሩም ይህ ፍላጎታቸው መቼም ሊሳካ እንደማይችል አሳይተናቸዋል ብለዋል።
ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ በመከፋፈል እርስ በእርሱ እንዳይተማመን ያደርግ እንደነበረ አውስተው የትግራይን ህዝብ ደግሞ የኢትዮጵያ ልጆች እየመጡብህና እየከበቡህ ነው እያለ ከወንድም የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በጠላትነት እንዲተያይ ሲሰራ የኖረ እኩይ ፖለቲካ አራማጅ ፀረ አገር ሃይል ነው ብለዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1